ፈውስ የምትፈልግ አገር

(በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ) – “አገዛዙ ስለ ተወጠረ መውጫ ቀዳዳ ለማግኘት ሲል ዕርቅና ድርድር እያፈለገ ነው።” የሚለው ከንቱ ማዘናጊያና የጊዜ መግደያ ትጥቅ አስፈች ሆኖ ቀርቷል። “ተጨፈኑና ላሞኛችሁ” የሚለው ዘዴ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቀርቶ፤ በጋርዮሽ ሥርዓት ለሚኖር ኅብረተስብ እንኳ አይሰራም። ኢትዮጵያን የያዛት በሽታ፤ ከገፋና ከደነደነ ደርጃ የደረሰ (አድቫንስድ ስቴጅ ላይ ያለ ) ነቀርሳ ነው። የነቀርሳ በሽታ እዚህ ደረጃ ከደረሰ፤ በቀድዶ – ጥገናም (ኦፔራሲዮን) ወይም በጨረር (ኬሞ ቴራፒ) የሚድን አይደለም። የበሽተኛውን ህይወት ማትረፍ የሚቻለው ነቅርሳውን አስወግዶ በመጣል ነው። ኢትዮጵያን ማዳን ካስፈለገ፤ መሠረታዊው መፍተሄው/ መዳህኒቱ፤ አብነቱ ምሥጢሩ፤ በሽታዋን ነቃቅሎ መጣል ያስፈልጋል። በመላው ዐለም የሚገኙ ተደናቂ ሐኪሞች፤ ቢሰበሰቡ፤ ሱባኤ ቢገቡ፤ ቢመክሩ፤ ቢዘክሩ፤ እየተወያዩ ቢከራከሩ ለሀገራችን መፍተሄ ሊያመጡ አይችሉም። ክኅሎትም ብልሃትም ዕውቀቱም ሆነ ኃላፊነቱ የወደቀው በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ነው። ይኽንን ግዴታ ለመወጣት፤ ለአንዴና ለመጨረሻ የሚሆን ርምጃ እንዲወስድ ያምናል። እርሱም ተበብሮ የጋራ ሀገሩ ጠላት የሆነውን ወያኔን በማስወገድ፤ በምትኩ ዴሞክራሲያ ሥር ዓተ- መንግሥት መመስረት ነው።  ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ