ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ያጎደሉት የአዲስ አበባ መስሪያ ቤቶች

(ግንቦት 05 ቀን 2009 ዓ.ም.) – ቴዲ አፍሮ የፖለቲካ ጥያቄ የሚያነሳ እንደ ወንጀለኛ መቆጠር የለበትም በማለት ተናገረ – ከጥር ወር ጀምሮ የነበረው የዝናም መቀነስ የምግብ እጥረቱን ያባብሰዋል ተባለ – በአዲስ አበባ አስተዳደር ስር ያሉ ከ232 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ ያጎደሉ መስሪያ ቤቶች ለገንዘቡ ጉድለት ምንም መግለጫ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ የሚለው የዘፈን አልበሙ ከስድስት መቶ ሺ በላይ የተሸጠለትና በዚህ ሳምንት በዓለም በርካታ አልበሞችን በመሸጥ በቢልቦርድ ዎርልድ ቻርት ላይ የአንድነኛነቱን ቦታ የያዘው ታዋቂውና ዝነኛው ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን) አሶስየትድ ፕሬስ ለተባለው የዜና ተቋም በሰጠው መግለጫ የፖለቲካ ጥያቄ ማንሳት ሃጢያት እንደሰራ ወንጀለኛ መቆጠር የለበትም ብሏል። ቴዲ ባደረገው ገለጻ ማንም ሰው ከፖለቲካና ከፖለቲካ ውሳኔ መገለል የሌለበት መሆኑን ገልጾ በዜጎች መካከል ግልጽ የሆነ ውይይትና ክርክር ያስፈልጋል ብሏል። የዜና ተቋሙ ቴዎድሮስ በዘፈን አልበሞቹ ውስጥ የተለያዩ ብሔረሰቦችን የሚያስተናግዱ ዘፈኖች ያካተተ በማንሳት ቴዎድሮስ ስለአንድነት የተናገረውንም ዘግቧል። ቴዲ ለዜና ተቋሙ በሰጠው ተጭማሪ መግለጫ መላውን አፍሪካ አንድ ለማድረግ ስትጥር የነበረች አገር አሁን በአንድ ድምጽ መናገር አቅቷታል ብሏል። ቴዲ በአብዛኛው የዘፈናቸው ዘፈኖች በአማርኛ ቋንቋ ቢሆንም ሌሎች ቋንቅዎችንም ደብለቅ አደርጎ በማስተናገዱ የአንድነት ድምጹን ከማስታጋባቱ በተጨማሪ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ሆኖለታል በማለት የዜና ተቋሙ ዘግቧል። ከዚህ በፊት በመኪና ሰው ገጭተሃል በሚል የሀስት ክስ 18 ወራት መታስሩንና ገጨበት የተባለው የፈጠራ መኪና ውስጥም ያልነበረበት መሆኑን ቴዲ መናገሩን የአሶስየትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ ገልጿል።

የወደፊቱን የረሃብንና የድርቅን ሁኔታ በመተንበይ ቀድሞ አድርጎ መረጃ የሚሰጠው ተቋም አርብ ዕለት በዘገበው መሰረት ከጥር ወር ጀምሮ በነበረው የዝናም መቀነስ ምክንያት በደቡብና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የምግቡ እጥረት እየተባባሰ መሄዱን ጠቁሟል። በተለይ በሱማሌ ክልል አካባቢ ያለው ቀውስ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችልና እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች መካከል ከፍተኛው ቦታ እንደያዘ ሊቆይ እንደሚችል ጠቁሟል። በአንዳንድ ቦታዎች የበልግ ዝናም መጠነኛ ቢሆንም በኦሮሞ እና በደቡብ አንዳንዳ አካባቢዎች የዘነመው ዝናም ከአማካይ በታች በመሆኑ ችግሩ ሊቀጥል እንድሚችል ጠቁሟል። ከረጅዎች የሚሰጠው እርዳታ የተረጅዎችን ችግር ለማቃለል ከሚያስፈልገው ወጭ በታች በመሆኑ እስከ ሚቀጥለው መስከረም ወር ድረስ በእርዳታ አሰጣጥ በኩል ከፍተኛ ውጥረት ሊኖር እንደሚችልም ተቋሙ አስረግጦ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ232 ሚሊዮን ብር በላይ በማጉደል በምርመራ ተድርሶባቸዋል የተባሉ በከተማው አስተዳደር ስር ያሉ ተቋሞች ስለሁኔታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማብራሪያ እንዲሰጡ ወያም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ቢሰጣቸውም ወደ ሶስት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ስለሁኔታው ገለጻ ሳይሰጡና ጉድለቱ እንዲስተካከል ሳይደርጉ ቀርተዋል በማለት የአገዛዙ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የማጭበርበር ግዥ መፈጸም፤ የገንዘብ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀስት ውል መዋዋል፤ ህጋዊ ባልሆነ ደረሰኝ ገንዘብ መክፈል እነ የመሳሰሉት የስርቆት ዘዴዎች የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች የተካኑበት ስለሆነ ምንም ዓይነት የጊዜ ገደብ ችግሩን የሚፈታው አይሆንም የሚሉ ዜጎች ስርዓቱ ካልተለወጠና ተጠያቂነት ካልሰፈነ ችግሩ አይፈታም ይላሉ።

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ዝርዝር ዜና ያዳምጡ