የክቡር ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ አጭር የሕይወት ታሪክ

ኮሎኔል  አስናቀ  እንግዳ ከአባታቸው ከአቶ  እንግዳ ገብረ ማርያም እና ከእናታቸው ከወ/ሮ  ውበቴ ገበረ ሥላሴ  በጎንደር ክphoto1ፍለሀገር፣  በደብረታቦር አውራጃ አየር ማርያም ደብር በጥር  7 ቀን 1906 ዓ/ም ተወለዱ።

ኮ/ል  አስናቀ ለውድ አገራቸው የነበራቸውን  ፍቅር፣ ኢትዮጵያዊ ወኔና ቁርጠኝነት ሀ ብለው የጀመሩት ገና በለጋ ዕድሜያቸው ነበር።  ጊዜው  ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን በግፍ የወረረበት  ስለነበር ወጣቱ አስናቀ  ወደ ጎንደር በመሄድ የጀግናውን የደጃዝማች አያሌው ብሩን ጦር ተቀላቅለው ለአገራቸውና  ለሕዝባቸው  ነፃነትና  ክብር በተደረገው መራር የአርበኝነት ተጋድሎ  ቀጥታ ተሣታፊ በመሆን  ጠላትን ተዋግተዋል።

አፄ ኃይለሥላሴ  ወደ ሱዳን መግባታቸው  ሲሰማ፣ ትንታጉ አስናቀ ወደዚያው  ተጉዘው ሶባ በተባለው ቦታ  ወታደራዊ ሥልጠና  የተሰጠውና  በሻለቃ (በኋላ  ጄኔራል)  ዌንጌት ይመራው የነበረውንና የጌዴኦን ኃይል በመባል ከታወቀው ልዩ የጦር ክፍል ጋር በመሆን ወደ አገራቸው ተመልሰው በመግባት አርበኞቻችን አገራቸውን ከጠላት  ነፃ ለማውጣት ባደረጓቸው የሞት የሽረት ፍልሚያዎች ተካፋይ ሆነው የኢትዮጵያን ትንሳኤ ካስገኙ አኩሪ የአገር ባላውለታዎች አንዱ መሆን በቅተዋል።   ሙሉውን ታሪክ ያንብቡ