ኮለኔል አስናቀ እንግዳ: ስራቸውን ጨርሰው ያረፉ ጀግና

ኢያሱ ዓለማየሁ – . . . ለጀግና አያለቅሱም ተብሏል። ጀግኖች ሞትን አይፈሩምና ዘጠኝ ሆኖ ቢመጣም አንድ በአንድ ግባ Colonel Asnake Engidaየሚሉ ናቸው። የጀግና ጀግና፤የወርቅ ዜጋ ምሳሌ የነበሩት ኮለኔል አስናቀ ስለ ታሪካዊ የሕይወት ሂደታቸው በመጽሃፍ አስፍረውታል። እኔ ስለ እሳቸው ማለት የምፈልገው በትግል ሜዳ በጎንደር ካገኘኋቸው ጀምሮ ለእኔ ለግሌ፤ ለድርጅቴ ለኢሕአፓ፤ ለኢትዮጵያና ለትግላችን ምን አንደምታና ሚዛን እንዳላቸው ምስክርነትን ለመስጠት ግዴታ ስላለብኝ ነው። ኮለኔል አስናቀ እኛ ኩታሮች ሳለን፤ ለንቃትም ለተቃውሞ ሰልፍም ገና ሳንበቃ ዛሬ ታሪክን ማጤን ያቃታቸው የሚያመስግኑትን የዘውድ አገዛዝ ተቃውመው፤ በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባር አጼውንም ለመገልበጥ የጣሩና የእስር ስቃይንም የተቀበሉ ናቸው። ወዳጃቸው ኮለኔል እምሩ ወንዴም ተመሳሳይ የሚያኮራ ታሪክ አላቸው። ሁለቱም በአጼው ስርዓት በደል ለደረሰበት ሕዝብ መብትና ብልጽግናን ለማምጣት መስዋዕትነትን የደፈሩ ናቸው። ከእነሱ በኋላ ነቃን አወቅን ብለን የተነሳነው ወጣቶች  አርአያ የሆኑልን ኮለኔል አስናቀና መሰሎቻቸው ናቸው። ኮለኔል አስናቀ የሀገራቸውን ድንበር ለማስከበርም በጦር ሜዳ የዋሉ ቆፍጣና መኮንን መሆናቸውም መጠቀስ ያለበት ነው።  ሙሉውን  ጽሁፍ ያንብቡ . . .