የአባያና የቻሞ ሀይቆች ሊደርቁ ይችላሉ

የፍኖተ ዴሞክራሲ ዜናና ኃተታ – የአባይና የቻሞ ሀይቆች ሊደርቁ ይችላሉ ተባለ – ከወያኔ ፖሊሲና ከአየር ጠባይ ለውጥ የተነሳ የቡና ምርት እንደሚያሽቆለቁል ተገለጸ – ወያኔ የኮሌራ በሽታ መስፋፋቱን አፍኖ መያዙ ተጋለጠ – ወያኔ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ የሚሸፍኑለት የውጭ ኃይሎች ናቸው ተባለ – የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የቴክኒካል ቡድን ጥናት ዘገባ መጠበቅ አለብን አሉ – የተባበሩት አረብ ኤምሬት በአገሩ አስሮ ሲያሰቃያቸው የነበሩትን የየመን ዜጎች ወደ አሰብ አዛወሩ።

በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ ቴክኒካዊ ጥናቶች፤ ታሪካዊ ግምገማዎችና የተለያዩ ምርምሮች ውጤቶች በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙት የአባያና የቻሞ ሀይቆች ሊድርቁ እንደሚችሉ የጠቆሙ መሆናቸው ሰሞኑን ተገለጸ። ላለፉት 55 ዓመታት

Abaya Lake
Abaya Lake

የተሰባሰቡት ልዩ ልዩ መረጃዎች በሃይቆች ውስጥ የፎስፈረስና የናይትሮጅን ንጥረ ነገሮች እየጨመሩ መምጣታቸውና እንዲሁም የውሓው ጥራት ቀስ በቀስ እየጎደለና እየደፈረሰ መምጣቱን ይጠቁማሉ። የውሃው ጥራት መጉደልና ድፍርስ እየሆነ መምጣት በውሃው ውስጥ ደለል እየተከማቸው መሄዱን ያሳያል ብሏል። ቀድሞ ከነበረው መሬት ውስጥ 39 በመቶ እንዲሁም በሳር ተሸፍኖ ከነበረው መካከል 37 ከመቶ የሚሆነው መሬት እየታረሰ በመምጣቱ ለመሬት መደርመስ ቀላል ከመሆኑ የተነሳ በወንዞች እየተያዘ ወደ ሃይቆች ውስጥ ሊገባ የቻለ መሆኑ ተነግሯል። በወያኔ ብልሹ አገዛዝ ስር እየደረሰ ባለው የደን ጭፍጨፋና የአካባቢ ደህንነት

Chamo Lake
Chamo Lake

ብክለት እንዲሁም በዓለም ላይ እየደረሰ ባለው የአየር ጠባይ ለውጥ የተነሳ የኢትዮጵያ የቡና ምርት በከፍተኛ ደረጃ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ተነገረ ። በዓመት በ አራት ዲግሪ ሲንቲግሬድ እየጨመረ ያለው ሙቀት የሚያመጣው የአየር መዛባትና በተጨማሪም ቡና ማምረት መቀነሱና የጫት ምርት መስፋፋቱ እንደ ምክንያት ከሚጠቁሱት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ። በርካታ የቡና ማምረቻ መሬቶች ለውጭ ኩባንያዎች መሰጠታቸውን የጠቀሱ ክፍሎች ሚሊዮኖች የሚተዳደሩበት የቡና ምርትና ሽያጭ ጉዳት ከደረሰበት የሚከተለው የኤኮኖሚ ቀውስ ቀላል አይደለም ብለዋል ። በአየር መዛባትም በኩልም በቅርቡ ሰፋፊ አካባቢዎችን የሸፈነው አንድ ጥናት ባቀረበው ዘገባ መሰረት በአየር ለውጥ የተነሳ ከ40 እስከ 60 ከመቶ የሚሆነው አሁን ያለው የቡና መሬት በምዕተ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ለቡና ምርት ተስማሚ እንደማይሆን ገልጿል። ከዚህ ሁኔታ ለመወጣት የሚችለው የቡና ማብቀልን ስራ ወደ ተራራማ አካባቢዎች ማዛወር ቢሆንም ይህም ከባድና የማይቻል ስራ እንደሆን ብዙዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም በወፍ ዘራሽ የሚበቅሉት የአረቢካና የሮበስታ የቡና ዘሮች ጭራሽ ሊጠፉ እንደሚችሉ ተገምቷል።

ቴድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በነበረበት ወቅት የነበረውን የኮሌራ በሽታ በመካድ ያለው የተቅማጥ በሽታ ብሎ እንደዋሸው ሁሉ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ረሃብ ባጠቃቸው አካባቢዎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ዜና እንዳይሰራጭ ወያኔ አፍኖ ይዞታል የሚል ክስ ቀርቧል። በደድብ ሱዳንና የመን መሰራጨቱ የተነገረው ኮሌራ በሶማሊያና በኢትዮጵያም ጨምሮ ከ 2100 ሰው በላይ መግደሉን ያረጋገጠው የፈረንሳዩ ድንበር የለሽ ሀኪሞች ተቋም በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ቦታዎች የሕጻናት ሞት ከረሃብና ከኮሌራ በሽታ ታይቷል ብሏል ። ሁኔታው እየከፋ እንጂ እየቀነሰ አይመጣም ያሉ ታዛቢዎች ወያኔ ባለው ዘረኛ ፖለቲካ መሰረት የሚጠላቸው ሕዝቦች ዘንድ ያለን ረሃብና ወረርሽኝ ቸል እንዳለው አቅርበዋል።

ወያኔ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ፍጹም የሆነ የአፈና አገዛዝ ካሰፈነ ጀምሮ በልዩ ልዩ ቦታዎች ግድያና ግፍን መፈጸሙ የሚታወቅ ሲሆን ትክክለኛ ቁጥሩን ለመደበቅ የሚያደርገው ጥረት በዓለም ደረጃ ባሉት ደጋፊዎቹና እንዲሁም ራሳቸውን ሰባዊ ኮሚቴ ነን በሚሉ አንዳድንድ ተቋሞች ከፍተኛ እርዳታና ትብብር መሆኑ እየተደረገለት መሆኑም ታወቋል ። ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለበት ወቅት ወያኔ ከ 3ሺ ያላነሰ ዜጎችን ገድሎ የሞቱት 700 መቶ ብቻ ናቸው በማለት ሲዋሽ ሌሎቹ ደግሞ የትግሉ እምብርት ወይም ዋና ቦታዎች ጎንደርና ጎጃም መሆናቸውን ክደው በኦሮሚያ 15 ሰው እንደተገደለና ከአማራው ክልል አንድ ሰው እንደሞት በመጥቀስ ሳያፍሩ መለጫ አውጥተዋል ተባለ። ወያኔ በያዘው ጸረ አማራ ፖለቲካውና ዘመቻው ተባባሪዎቹ በርካታ ናቸው ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች የዚህ መንሰኤው አማራ ከተመታ ኢትዮጵያ ያበቃላታል የሚለው ድምዳሜ ነው ብለዋል። ወያኔ በጎንደር ጎጃም የጠነከረ አፋኝ ዘመቻ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ከዚህ በፊት ተጋልጧል።

በዘር ኤርትራዊ የሆነውንና ለረዥም ጊዜ በኢኮኖሚ አማካሪነት የአገዛዙ ዋና አገልጋይ የነበረው ንዋይ ገብረአብ ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ጉዳይ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት በወያኔ እጩ ሆኖ መቅረቡ ይታወቃል። እየተካሄደ ካለው የአፍሪካ ህብረት አካባቢ በመጨረሻ የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው የማዳጋስካሩ ዕጩ ቦታውን የወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና በዚሁ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት የግብጹና የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገናኝተው መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በዚሁ ግንኙነት ላይ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአጥኝ ቡዱኖቹ ዘገባ ሳይጠናቀቅ ግድቡን ውሃ መሙላት ግብጽ ተጠቂ ሊያደርግ እንደሚችል የጠቆሙ መሆናችው ታውቋል። ባለስልጣኑ አጥኝ ቡድኖቹ ዘገባውን እስኪያቀርቡ ድርስ መቆየቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው እስከዚያው በመጀመሪያ ዘገባቸው ላይ የተጀመረው የሶስቱ አገሮች ውይይት እንዲቀጥል ጠይቀዋል። አጥኝ ቡድኖቹ ሥራቸው ያጠናቅቃሉ የሚባለው በሚቀጥለው ዓመት ህዳር ወይ ታህሣስ ወር ከጥቂት ቀናት በፊት ሲሆን የወያኔው የመስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ተብየው የአጥኝ ቡድኖቹ ዘገባ መጣም አልመጣም የግድቡ የግምባታ ስራ እንዳለቀ ውሃ የሚሞላ መሆኑ መናገሩ ይታወሳል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ባለስልጣኖች ሽብረተኛ ናቸው በሚል በአገራቸው አስረዋቸው የነበሩ የመን ዜጎችን ከሻዕቢያ በተከራዩት አሰብ ወደ ሚገኘው ጦር ሰፈራችው ማዛወራቸው ተጋልጧል። በዚሁ የአሰብ የጦር ሰፈር እስር ቤት ውስጥ በየመኖቹ ላይ ግብረ ስየል እየተፈጸመ መሆኑን ያጋለጡ ውስጠ አዋቂዎች ሻእቢያ ለዚህ ግልጋሎቱ ለአሰብ ከሚከፈለው በዓመት 500 ሚሊዮን ዶላር በተጭማሪ ተከፍሎታል ብለዋል ። በሻዕቢያ አቅራቢነት ኤሚሬትና ሳውዲ አረቢያ ለጸረ ወያኔ ነን ባዮች ቡድኖችን እርዳታ እንዲሰጡ የተደረገው ሙከራ ግን እስካሁን አልተስካም የሚል ዘገባም ቀርቧል።

ዝርዝር ዜና ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ያንብቡ