ህይወት አያሌው (1951- 2009)

ህይወት አያሌው በ1951 ጎንደር ከተማ ተወልዶ አንደኛና ሁለተኛ ትምህቱን በዱሮው ቀዳማዊ አሁን ፋሲለደስ በሚባለው hiwotትምህርት ቤት አጠናቅቋል። ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት በእድገት በሕብረት ሁመራ ከመዝመቱም በላይ፣ በነበረው የትግል ተሳትፎ በቀይ ሽብር ጊዜ በሃታ እስር ቤት ለሶስት አመታት በእስር ተሰቃይቷል። በደረሰበት ግርፊያ ምክንያትም ለረዥም ጊዜ የእግር ህመምተኛ ሆኖ ቆይቷል። 1978 ዓ.ም ወደ ሱዳን ተሰዶ በዚያ የሚገኘውን የኢሕፓን ቅርንጫፍ በመቀላቀል ትግሉን ሲያካሄድ ቆይቷል። በሱዳን ካርቱም በመምህርነት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን በካምቦኒና በኢትዮጵያዊያን በተቋቋሙ የተለያዩ ት/ ቤቶች አገልግሏል። ባንድ ወቅት የመኪና አደጋ አጋጥሞት ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ቆይቷል። ህይወት በእምነቱ እንደፀና በሐምሌ 8 ቀን 2009 አርፎ በዛኑ ዕለት የቀብሩ ሰነ ስርዓት ተፈፅሟል። ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለጓዶቹ መፅናናቱን ይስጣችሁ እንላለን።