የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ …………. ታዲያ ዛሬ ሁሉም፤ በበኩሉ፤ “ይታደሏል እንጅ ይታገሏልን? ” እያለ የአግራሞት ጥያቄ እየጠየቀ ራሱን እያጽናና መቆየትን መርጧል ብንል፤ ስህተት ነው ሊባል የሚችል አይመስለንም።  ምናልባት፤ እራስን እያጽናኑ መኖር አይከፋም ይሆናል፤ እራስን እያታለሉና እየደለሉ መቆየት ግን፤ ዉሎ አድሮ፤ አሉታዊ አስተጋቦን እንጅ፤ ፋይዳን አያስገኝም።  እንዲያውም፤ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” የሚል የለበጣ ፈገግታን ያስከትላል።  የማነኛውም ኅረተሰብ፤ ከዝቅተኛው ዕርከን የመድረስ ምልክቱ፤ ተስፋ ቢስ መሆኑ ነው።  የሀገራችንም ሕዝብ ዛሬ የደረሰለት ነፃ አውጭ ኃይል በማጣቱ፤ ተስፋውን ቢቆርጥ ይታዘንለት ይሆናል እንጅ አይፈረድበትም።  ለአምሣ ዓመታት ያህል፤ በተፈራራቂ ጨካኝ አምባገነኖች መገዛት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚሸከመው በላይ ሆኖበታል።  ነገር ግን፤ “እስኪያልፍ፤ ያለፋል” ቢል፤ “አየ፤ ትለፋለህ እንጅ፤ ምን ያልፍልኻል?” ሊባል አይገባውም።  ይኽንን ምፀት፤ መስማት የሚፈልግ ህዝብ አይደለም። ሙሉውን  ሀተታ ያንብቡ