ሥጋ የሰረቀ፤ በመረቅ ይያዛል!

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ: ኢትዮጵያ ሀሳቡዋ ብዙ ፤ ችግሯ ውጥንቅጥ፤ ታሪኳ ውስብስብ፤ ዜጎቿ ቅይጥ-ጉራማሌ፤ ምሥጥሯ ጥልቅ፤ መልከዐ ምድሯ ዥንጉርሩና ወጣ-ገባ፤ መሆኗንና የነዋሪዎቿንም ሥነአዕምሮና መስተጋብር በሚገባ ሳያውቁ፤ ሳይረዱ፤ ሳያጤኑ፤ ሳይማሩ ሳይመረምሩ፤ እንዲያው በችኮላ፤ በሀገርና በሕዝብ ጉዳይ ዘው ብሎ መግባት፤ ከማይወጡበት ማጥ ውስጥ ግብቶ ራስን ማጥፋት ይሆናል። ኢትዮጵያ አትንኩይ ባይ ሀገር ነች። ዜጎቿም ለነፃነታቸው ቀናዒ ናቸው። ይኽንን ሃቅ ማወቅ አስፈላጊም ግዴታም ነው።  ሙሉውን  ሀተታ ያንብቡ . . .