ሰይጣናዊ ቅናት፤ የተልባ ስፍርና ዘመናዊ ከንቱዎች

ከሀማ ቱማ – . . . በሁሉም ጊዜ ግን የእናት ሆድ ዝንጉርጉር እንዲሉ ጀግናም ባንዳም ሀገራችን ትወልዳለችና በአሁኑ ጊዜም ዘመናዊ ባንዳዎችን-ከንቱዎችንና በዚያውም ለሀገር የሚሰዉ ጀግኖችንም አፍርታለች። ከንቱዎቹ በራሳቸው፤ በኢትዮጵያ፤ በሕዝብ ላይ እምነት ጎድሏቸዋልና ሳይታገሉ የተሸነፉ፤ እጅ የሰጡና ለክህደትም የቀረቡ ናቸው። አድርባይነት፤ ፍርሓትና ተልባ ስፍር መሆን ይገልጻቸዋል። መዋለል፣ ሳይታገሉ መሸነፍ። የኢትዮጵያ ድርጅቶች ሁሉ በወያኔና ሻዕቢያ ተፈጠሩ ብለው የሚያምኑት የሽንፈትና ዝቅተኝነት ስሜት ስለወጠራችውና  ገንጣዮቹ ገዝፈውባቸዋልናም ነው። ነውናም የታገሉትን በማውገዝ ብስጭታቸውን የተወጡ ይመስላቸዋል። በደርግና በወያኔ ላይ ከመዝመት ይልቅ እነዚህን አረመኔዎች ቆርጦ የታገለውንና በመታገል ላይ ያለውን ማውገዙ ይቀናቸዋል። ራስ ጥላቻ ይሏል ይህ ነው። ትግሉ ሳይጀመር መውደቅ፤ መሸነፍ። ወያኔ ሀገራቸውን የከዱትን የትግራይ ተወላጆችና መሰል ሌሎችንም ይወክላል። መድረክ ያጣበቡ ቅጥረኞቹም በዚህ ክህደት ተጠቃለው የሚወገዙ ናቸው። ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ጸረ ወያኔና ኢትዮጵያዊ አቋምን ይዞ ለ26 ዓመት የወያኔና ሻዕቢያን ሴራ ሲቋቋም ቆይቷል። ይህ ነው ለኢትዮጵያ ስርየት ተስፋ የሚሰጠንና ድላችን እንዳይቀማ ጸንተን እንገኝ ብለን ለመጥራት የግድ የሚለን። ኢሕአፓ ግዳጁን በመወጣት ላይ ነው።  ሙሉውን ያንብቡ …