የውጪ ምንዛሪ ኦና መሆን የወያኔን የደም ስሮች እየገደለ መሆኑ ተሰማ

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ – ህፃናት ገዳዩ ወያኔ፣ የህፃናት ቀንን ማክበሩ አነጋጋሪ ነው ተባለ – የውጪ ምንዛሪ ኦና መሆን የወያኔን የደም ስሮች እየገደለ መሆኑ ተሰማ – የወያኔ ፓርላማ ወና እየሆነ መሄዱ ተጋለጠ – የኮካ ኮላ ኩባንያ ስኳር መዘረፉ ታወቀ – ከቻይና ውዳቂ የሆኑ የኤች. አይ.ቪ. መመርመሪያ ቁሶቁሶች ግዢ መፈጸሙ አነጋጋሪ ሆኗል – ወያኔ ከኳታር ጋር መፈጣጠሙ መዘዝ አለው እየተባለ ነው።

ህፃናት ገዳዩ ወያኔ፣ የህፃናት ቀንን ማክበሩ አነጋጋሪ ነው ተባለ

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት በከተሞች በልመና፣ በጣም ዝቅተኛ በሆነ የጎዳ ላይ ንግድ እየተራወጡ ባሉበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ትምህርት እንዳያገኙ በሆኑበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት በተለያዩ በሽታዎች እየማቀቁ ባለበት የዓለም የህፃናት ቀን በወያኔ አጋፋሪነት መከበሩ ገድሎ መቆንጠጥ ነው ተብሏል፡፡ ዛሬ ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህፃናት በመላው ኢትዮጵያ በወላጆቻቸው ድህነት ምክንያት ወይ ለልመና፣ ወይ ህፃናቱ በእራሳቸው እየተራወጡ የእለት ጉርሳቸውን ሲቃርሙ እንደሚውሉ የሚታወቅ በመሆኑ በርካታ የፖለቲካ አዋቂዎች ወያኔን በህፃናት ገዳይነት ይከሳሉ፡፡ ሕዝባዊ አመጾች በተካሄዱባቸው በርካታ አካባቢዎች የወያኔ የክብር ዘብ የሆነው አረመኔው አጋዚ ጦር በርካታ ወጣቶችን በአልሞ ተኳሾት በመግደሉ ወያኔን የህፃናት ገዳይ ያደርገዋል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በሻገርም ወያኔ በጉዲፈቻ ስም ህፃናትን እንደ ሸቀጥ እየቸበቸበ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ ሕህፃናት ለአደንዛዥ እጽ ሱሰኝነት ተጋልጠዋል፡፡ ወያኔ የእናቶችንና የህፃናትን ሞትን መቀነሱን ለፖለቲካ ተረፌታ ቢለፍፍም ሀቁ ተወልደው ሁለተኛ አመት ልደታው ሳይሞላ የሚቀጠፉ ህፃናት ቁጥርን ቤት ይቁጠረው የሚያሰኝ ነው የሚሉ ብዙዎች መሆናውን ተገንዝበናል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተከበረው የዓለም ህፃናት ቀን በህፃናት ገዳዩ በወያኔ ሊከበር አይገባውም ነበር ተብሏል፡፡

የውጪ ምንዛሪ ኦና መሆን የወያኔን የደም ስሮች እየገደለ መሆኑ ተሰማ

በብሔራዊ ባንክ ለመጠባበቂያ ተይዞ የነበረው የውጪ ምንዛሪ በተለያዩ የወያኔ ቁንጮዎች ተሟጦ በመወሰዱ በአሁኑ ወቅት አንድም ዓይነት የውጪ ንግድ መፈጸም ፈጹም እማይቻልበት ደረጃ መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡ በውጪ ምንዛሪ እጥረት የባህር ትራንስፖርት ድርጅት እንቅስቃሴ እየተሽመደመደ መሆኑ ተጋለጧል፡፡ ለህይወት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድሀኒቶች በውጪ ምንዛሪ እጥረት ሰበብ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ማቆማቸው በስፋት ይወራል፡፡

የወያኔ ፓርላማ ወና እየሆነ መሄዱ ተጋለጠ

የወያኔ ፓርላማ ወንበሮች በየጊዜው በአብዛኛው ቦዶ ሆነው መታየታቸው የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የወያኔ ፓርላማ አባላት በዛት ከግማሽ በታች መውረዱ የወያኔ አባላት የእርስ በእርስ መናቆር ውጤት እንደሆነ ታጋለጠ፡፡ ከአምስት መቶ አራባ ሰባት አባላት ውስጥ ግማሹ እንኳ አለመገኘቱ የወያኔ መሰነጣጠቅ ምልክት መሆኑን የሚያስረዱ ብዙዎች ናቸው፡፡

የኮካ ኮላ ኩባንያ ስኳር መዘረፉ ታወቀ

የስኳር እጥረት በርካታ ቀውስ እያስከተለና ህብረተሰቡን ለግጭት እየዳረገ መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ የኮካ ኮላ ፋብሪካ ባህር ዳር ለሚገኘው ፋብሪካው በአራት ካሚዮን ሰባት መቶ ሃያ ኩንታል ስኳር ሰሜን ሸዋ፣ ጎሀ-ጽዮን፣ ከአዲስ አበባ አንድ መቶ ሰማንያ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኘው ወረ ጃርሶ ወረዳን አቋጠው እንዳያልፉ በአካባቢው የፖሊስ ኃይሎች መታገታቸውና ስኳሩም እንዲራገፍ መደረጉ ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታ ከደረሰው የስኳር እጥረት ጋር በተያዘ የተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አነጋጋሪው ጉዳይ ግን የድርጊቱ ፈጻሚዎች የደምብ ልብስ የለበሱ የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች መሆናቸው የወያኔ የእዝ ስንሰለት እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚሳይ ነው ተብሏል፡፡

ከቻይና ውዳቂ የሆኑ የኤች. አይ.ቪ. መመርመሪያ ቁሶቁሶች ግዢ መፈጸሙ አነጋጋሪ ሆኗል

የኤች.ኤ.ቪ. ስርጭት እንደ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተስፋፋ ባለበት ወያኔ ደረጃቸው ዝቅ ያሉ የበሽታው መመርመሪያ ማሳሪያዎች ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም ውዳቂ መሆናቸው ተጋለጠ፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች ያቀረበው ቤጅንግ ዋንቲ ባዮሎጂካል ኢንተርፕራዝ የተሰኘ ድርጅት ሲሆን የቀረቡት የኤች.ኤ.ቪ መመርመሪያ መሳሪዎች ደረጃቸው በእጅጉ ዝቅ ያሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት እንደዚህ የመሰሉ የቻይና የንግድ ድርጅቶች እንዲህ ያሉ ውዳቂ ሸቀጦችን ለማቅረብ የሚያደፋፍራቸው ምን ጊዜም ከጀርባቸው ያሉት የወያኔ ቁንጮዎች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች በደረጃቸው እጅግ የወደቁ መሆናቸው ተሰማ

ወያኔ የሀገራችንን የትምህርት ጥራት እመቀ እመቃት በመክቱተቱ በሀገር አቀፍ ደረጃና በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እየወረደበት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በቅርቡ በትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥን አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ይፋ እንዳደረገው ዘጠና አራት ከመቶው የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥ ደረጃቸው ከመደበኛው መስፈርት እጅግ በጣም የወረደ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የወያኔ ቁንጮዎች በገንዘብ የተገዙ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪዎች ባለቤት በሆኑባት ሀገር ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ ትምህርት እየተልከሰከሰ እንጂ እየጠራ አይሄድም ተብሏል፡፡

ወያኔ ከኳታር ጋር መፈጣጠሙ መዘዝ አለው እየተባለ ነው

ይህ የወያኔና የኳታር ጋብቻ የፖለቲካ እንደምታ እንዳለው በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ በሳዑዲና በግብፅ የሚሽከረከሩት የባህረ-ሰላጤው ሀገራ ኳታርን ማግለላቸውና በአሸባሪው አይ ሲ ስ እረዳትነት መወንጀሏ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ሳቢያ ኳታር አሰብ ወደብ ያሰፈረችውን ጦሯን ማስወጣቷ የሚታወቅ ነው፡፡ ወያኔ የውጪ ምንዛሪ እጥረቱን ለመቅረፍ በሚል ጭፍን አስተሳሰብና የግብፅን ተጽእኖ መቋቋም እንዲያስችል በሚል ከኳታ ጋር የጭፍን የተደረገው መፈራረም ሳይደርቅ ከሳዑዲና ከሸሪኮቿ ወያኔን ቀስፎ የሚይዝ ተጽእኖ እንደሚያደርሱ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ለዝርዝር ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮን ያዳምጡ