የዓባይ ግድብ መዘዙ አይቀሬ ይመስላል

ፍካሬ ዜና (ህዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም.) – የዓባይ ግድብ መዘዙ አይቀሬ መሆኑ ተሰማ – የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠና እየታፈነ መሆኑ ተነገረ – የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠና እየታፈነ መሆኑ ተነገረ – በአዲስ አበባ የህዝብ የመጓጓዣ አገልግት አሳዛኝ ነው ተባለ – የወያኔ/ህወሀት መቆራቆዝ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል እየተነገረ ነው – በጋምቤላ፣ የገቢዎች ጽህፈት ቤት በእሳት መጋየቱ ታወቀ – “የድንበር ግጭት” የተባለው አገርሽቶ የንፁሀን ህይወት መቅጠፉ ተሰማ  – በተለያዩ ዩኒቭርሲቲዎች ትምህርት መቋረጡ ታወቀ።

የዓባይ ግድብ መዘዙ አይቀሬ መሆኑ ተሰማ

ወያኔ በጭፍን የሕዝብ ድጋፍን ባቀላሉ ለመሸመት እንዲያስችለው በሚል ዓባይን የመገደብ ዘመቻው እስካሁን ባለው ሂደት ከቃላት ጨዋታ ያልዘለለ መሆኑን ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ በተለይ በግብፅ በኩል በተደጋጋሚ፣ በተለያዩ ኃላፊዎች የሚሰነዘረው ኃይለ-ቃል ያዘለ መሆኑ እያደር እየዋለ የሚያስከትለው ጦስ ሊኖር እንደሚችል የሚገመት ነው ተብሏል፡፡የግብፁ ጄነራል አል ሲሲ በቅርቡ አንድ የአሳ እርባታ ጣቢያን ሲመርቁ ባደረጉት ንግግር የዓባይ ውሀ ለግብፅ “የሞትና የህይወት ጉዳይ” መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን በርካቶች የማስጠንቀቂያ ደወል እያሉት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ወያኔ የሱዳኑ በሺርን ሀገርን እየቆረሰ በመስጠት ሊደልለውና ከጎኑ ሊያሰልፈው እየሚከረ ቢሆንም የሱዳኑ መሪ፣ በዚህ ወቅት የፖለቲካና የኤኮኖሚ ቀውስ አላፈናፍን ስላለው ወያኔን ወግኖ ለግብፅ ጀርባውን ይሰጣል ተብሎ አይታሰብም ተብሏል፡፡ ይህ ሁኔታ እየተወጠረ ሄዶ መበጠሱና ቀውስ ማስከተሉ አይቀሬ ነው እየተባለ ነው፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠና እየታፈነ መሆኑ ተነገረ

የኢንተርኔት አግልግሎት አቅራቢ የሆነው ብቸኛው ቴሌኮም የተሰኘው መንግስታዊ ድርጅት ሲሆን ይህ ድርጅት በየጊዜው የኢንተርኔት አገልግሎትን ይቆርጣል፡፡ በቅርቡ በአፍሪካ ደረጃ በደንበኛ ብዛት አንደኛ መውጣቱ የተነገረ መሆኑ ብዙዎችን አበሳጭቷል፡፡ ብቸኛ የኢንተርኔትና የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልሎት አቅራቢ ሆኖ እንኳ በአፍሪካ በዓለም ደረጃ ቢሆንም ኤስደንቅም የሚሉ ብዙዎች መሆናቸውን ተረድተናል፡፡ ይህ ድርጅት በየጊዜው ከደምበኞች ሂሳብ ላይ እየመነደፈ የወያኔን ካዝና እንደሚሞላ የሚታወቅ ነውም ተብሏል፡፡ እውነት ከተነገረ ቴሌኮም የተሰኘው ድርጅት በዓለም ከሚገኙ የኢንተርኔትና የሞባል ስልክ አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች ከቀዳሚ ወንጀለኛ ሆኖ ለፍርድ በቀረበ ነበር ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ የህዝብ የመጓጓዣ አገልግት አሳዛኝ ነው ተባለ

ወያኔ አዲስ አበባን ዘመናዊ ከተማ ማድረጉን በተለያዩ ጊዜያት ማቅራራቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ሀቁ ግን አዲስ አበባ ወደ ኋላ እየተጓዘች መሆኗ ነው፡፡ የሕዝብ የመጓጓዣ አገልግሎቶች ስርዐት መዘርጋ ባለመቻሉ ምክንያትና በሥራው ላይ የተሰማሩ በወያኔ በሚደርስባቸው ወከባ ምክንያት ሥራቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማከናወን እንደታሳናቸው እየተስተዋለ ነው ተብሏል፡፡ በመጓጓዣ ችግር ሳቢያ ወደ ሥራ የሚጓዙና ከሥራ ወደ ቤታቸው የሚመለሱ የአዲስ አበባ ኗሪዎች አብዛኞዎቹ ከሦስት ሰዐት በላይ ታክሲ ወይም አውቶብስ በመጠበቅ ጊዜያቸው እንደሚቃጠል ለማወቅ ተችሏል፡፡ በከተማዋ ተጀመረ የተባለው የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት እንደው የይስሙላ መሆኑ እየተስተዋለ ነው ተብሏል፡፡ ይህ የባቡር አገልግሎት የሚባለው ባለ አንድ ፉርጎ በመሆኑ የተጓዡ ሕዝብ ብዛት ሊነገር ከሚገባው በላይ በመሆኑ ተጓዦች እጅግ ተጨናንቀው በመጓዛቸው ጉዞውን ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ያደርገዋል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህም የባር አገልግሎ በከተማዋ በሁለት አቅጣጫ ብቻ ሲሆን በጉዞ ላይማ በኤሌክትሪክ መቋረጥና በባቡሩ ብልሽት የሚቆምበት ጊዜ እንደሚበዛ አገልግሎቱን እየተጠቀሙ ያሉ መንገዶች በምሬት ያስረዳሉ፡፡ የዛሬ ሁለት አመት ከሽሮ ሜዳ እስከ ስቴድየም ግንባታው እንደሚጀምር የተነገረው የባቡር ሀዲድ የውሀ ሽታ ሆኖ መቅረቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ወያኔ ለባቡሩ ግንባታ ከቻይና የተበደረውን መክፈል ባለመቻሉ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የባቡሩ አገልግሎት የቻይና መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ይህ ከቻይና የቅኝ አገዛዝ ስልት አንዱ መሆኑ እንደሆነ በርካቶች ያስረዳሉ፡፡

የወያኔ-ህወሀት መቆራቆዝ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል እየተነገረ ነው

ወያኔ ከአንድ ወር በላይ ሲቆራቆዝ ከርሞ ለጊዜው የመሰሪው የስብሀት ቡድን በተቀናቃኙ በዓባይ ወልዱ፣ በአዜብ ፣ በሳሞራ በሚመራውን ቡድን ላይ የበላይነቱን ያገኘ ይመስላል፡፡ ሁለቱም አንጃዎች የሀገር ጠንቆች፣ የሕዝብ ጠላቶች፣ የሕዝብ ሀብት ዘራፊዎች መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የሰብሀት ቡድን የዐባይ ወልዱ ቡድንን በዝምድና ሐረግ የሚሠራ ብሎ እንደወነጀለው መነገሩ የሚታወስ ሲሆን በቅርቡ ከተሸሙት የሕወሀት ምክትልነት ኮርቻ ላይ የወጣችው ፈትለወርቅ የተባለችው የስብሀት ነጋ የወንድም ልጅ መሆኗ አንዱ በአንዱ ላይ ጣቱን ሲቀስር እንዲህ የፏለሉባት ጀንበራቸው እየጠለቅች ነው የሚሉ ብዙዎች መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡ የህወሀት መሪነትን የተሾመው ደብረ-ጽዮን የተባለውም ላፉ ለከት የሌለው ተራ ስድ፣ ተሳደቢ፣ በቅርብ የሚውቁት እንደሚሉት አስተሳሰቡ ከቅል አንገትም የጠበበ እንደ ሆነ ያስረዳሉ፡፡

በጋምቤላ፣ የገቢዎች ጽህፈት ቤት በእሳት መጋየቱ ታወቀ

በጋምቤላ ከተማ ህዳር 16 ቀን በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የጋምቤላ የገቢዎች ጽህፈት ቤት መቃጠሉና የተለያዩ ሰነዶችና ንብረቶች አመድ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አደጋውን አስመልክቶ ኃላፊነቱን የወሰደ ኃይል ባይሰማም ጉዳዩ በቀጥታ ሊያያዝ የሚችለው ወያኔ በጣለው በቅጡ ያልተጠና የግብር ጫና ሊሆን እንደሚችል በርካቶች አስተያየታቸውን እየሰነዘሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋምቤላ የበጀት እጥረት በመከሰቱ የመንግስት ሠራተኞች የመስከረም ደሞዝ የተከፈላቸው በዚህ በህዳር ወር መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ይህ በጋምቤላ የተከሰተው የገንዘብ እጥረት አጠቃላይ በሀገሪቱ የተከሰተው የመዋዕለ ንዋይ ቀውስ ውጤት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

“የድንበር ግጭት” የተባለው አገርሽቶ የንፁሀን ህይወት መቅጠፉ ተሰማ

ሰሞኑን በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱ ግጭቶች ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፉ ታወቀ፡፡ ረቡዕ እለት በጉሱም ወረዳ በተከሰተው ግጭት በወያኔ ጦር ወደ አምስት የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውና ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ ለግጭቱ ምክንያት እንደሆነ ከአካባቢው ኗሪዎች የተገኘው መረጃ እንደሚስረዳው አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ በሶማሌ ልዩ ኃይል በመገደሉ ነው ተብሏል፡፡ ህዳር አስራ አምስት ቀን በአሬሮና በመልካ ሀልቱ የሶማሌ ልዩ ኃይል በከፈተው የእሩምታ Commented [QN2]: ተኩስ ከአስራ ሦስት ሰዎች በላይ የተገደሉ ሲሆን ወደ ያሃ አምስት የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ህዳር ሃያ በናዝሬት ቤት ለማፍረስ ከተሰማራው የወያኔ ኃይል ጋር ሕዝቡ ግብ ግብ በመፍጠሩ አንድ ሰው በጽኑ የቆሰለ መሆኑ ሲታወቅ ሕዝቡ ሁለት የፖሊስ የሞተር ብስክሊቶችን በእሳት ማጋየቱ ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን የሚቀፈቅፈው ግጭቶችን በማብረድ ስም ከሰልጣን ኮርቻው ላለመፈነገል መሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡

በተለያዩ ዩኒቭርሲቲዎች ትምህርት መቋረጡ ታወቀ

ዘንድሮ እስከዚህ የአመቱ የትምህርት ዘመን ሦስተኛ ወር እየተጠናቀቀ እስከ አለበት ድረስ በበርካታ ዩኒቭርሲቲዎች ኮስተር ባለ ሁኔታ ትምህርት እተካሄደ አለመሆኑ ታውቋል፡፡ በተለይ በጂማ፣ በአምቦ፣ በአርሲ፣ በሀሮማያ፣ ዩኒቭርሲቲዎች የተማሪዎቹን ተቃውሞ ለማፈን ወያኔ በየግቢዎቹ ውስጥ አጋዚ የተባለው የክበር ዘብ ጦሩን በማስፈሩ የወያኔ ጦር ከግቢያቸው ለቆ እንዲወጣ በመቃወም ትምህርት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸው ከየስፍራው የደረስን መረጃ ያስረዳል፡፡ ለዚህ የተማሪዎች ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያት ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንዲቀመቱ በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረት ውጤታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ተማሪዎች ዲግሪያቸውን ይከለከሉና የሚሰጣቸው አድቫንስድ ዲፕሎማ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ የትምህርት ጥራት በመመዘኛ ፈተና የሚመጣ አለመሆኑን በመግለጽ፣ የትምህርት ጥራት አጠቃላይ የስርዐተ-ትምህርት ስር-ነቀል ለውጥ እንደሚተይቅ ያስረዳሉ፡፡ ይህ የተጀመረው የተማሪዎች አመጽ በመላው ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚቀጣጠል በርካቶች ግምታቸውን ይሰነዝራሉ፡፡

ዝርዝር ወቅታዊ ዜና ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ያዳምጡ