ፖለቲካዊ ፍርድ የሙስሊሙን ሰላማዊ ትግል አይገታውም!

ኢሕአፓ: ከጥቂት ቀናት በፊት ለተወሰነ አመታት በእስር ቤት በወያኔ አገዛዝ ታግደው የነበሩት የ”ድምፃችን ይሰማ” የሕዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችን ለሶስት አመት በእስር ቤት በሕገ ወጥነት ማጎር ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ በደሎችም ዳርጓቸው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።  በሕዝቡ ባጠቃላይ በተለይም በክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን ለማስጠላት በፊልም የተቀረፀ የጥላቻ ዘመቻ በራሱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር ባደረጋቸው የመገናኛ ተቋማት አማካኝነት ሲነዛባቸው የነበረ መሆኑም አይረሳም።  በቅርቡ በሃምሌ 27 ቀን የዚህ አስደንጋጭና አሳዛኝ ተውኔት የመጨረሻው ትዕይንት በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙትንና ለእስር በዳረጋቸው የኮሚቴው መሪዎች ላይ ከ 7 እስከ 22 አመት የሚደርስ ፖለቲካዊ የእስር ብየናውን በካድረዎቹ ዳኞች ማስፈረዱን ይፋ አድርጓል።  በዚህም ራሱ በራሱ በማንም ቅን ኢትዮጵያዊ ዜጋና ሰላም ወዳድ በሆነ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ሁሉ የሚወገዝ መንግሥታዊ ሽብርተኛነቱን አረጋግጦበታል።  ሙሉውን ያንብቡ