ሕዝባዊ ትግልና የሽግግር ጥያቄ

ዴሞ (ቅጽ 43፣ ቁ.4 መጋቢት/ሚያዚያ 2010 ዓ.ም) . . .  በአዲሱ የወያኔ መሪ አማካኝነት በርካታ የአስተዳደር ለውጦችና መስተካከሎች እንደሚደረጉ፤ የተሟላ ዴሞክራሲ እንደሚኖር፤ ነጻ ምርጫ በተግባር እንደሚውል፤ …ወዘተ እየተለፈፈ በሌላ በኩል በኮማንድ ፖስት አማካይነት ታጋዮች እየተለቀሙና እየተገደሉ ትግሉን ለማኮላሸት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ እያየን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው በዚያው በድርጅቱ የተሰየመ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም የሥልጣን ሽግግር ተደረገ በሚል ከበሮ እየተደለቀ፤ በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ምርጥ ምርጥ ቃሎች በመጠቀም ያልሆነ ተስፋ እየተሰጠ፤ አባላት በአዲስ መልክ እየተመለመሉ፤ በዲያስፖራው ሳይቀር ይህንን ጉዳይ የሚያሳኩ ክፍሎች ተልእኮ እየተሰጣቸው የሕዝብን የትግል መንፈስ ለማሸሽ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በሌላ በኩልም የወያኔው ቡድን ድርጅታዊ አቋሙን እያጠናከረ፤ ለጥቅም ያደሩትን በአዲስ መልክ እየመለመለ፤ በወታደሩና በጸጥታው በኩል ተከስቶ የነበረውን ክፍተት እያሟላ ለሌላ ዙር የአምባገነን አገዛዙ ሁኔታውን እያመቻቸ መምጣቱ የሚታይ ሆኗል። በጻዕረ ሞት ላይ የሚገኘው አገዛዝ የኋላ ኋላ መወገዱ የማይቀር ቢሆንም፤ በሚወስዳቸው ጥገናዊ የማስመሰያ ለውጦች የዜጎችን አስተሳሰብና አስተያየት ለማስለወጥና ከትግሉ ለማዘናጋት በከፍተኛ ደረጃ በሁሉም መስክ እየጣረ ነው። ሙሉውን ያንብቡ . . .

pdf_print