በሽግግር ሂደት እንታደግ !


ዴሞ ቅጽ 45 ቁ. 1፣ ነሐሴ 2011 / መስከረም 2012 (የኢሕአፓ ልሳን ) – ዛሬም ለውጥ የለም ስንል ያለፈው እንዳይደገም ማለታችን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ “ተቀመጥ በወንበሬ ተናገር በከንፈሬ” ብሎ የሰየመው የራሱ የሆነ ሕዝባዊ መንግሥት አልመሠረተም፤ የሥልጣኑ ባለቤት አልሆነም ማለታችን ነው። ዛሬም ጸጥታው፥ ጦሩና ቢሮክራሲው፥ … ወዘተ ሙሉ በሙሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ሥር ናቸው። ዛሬም አገራችን በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ማጎሪያነቷ እንደቀጠለ ነው።ዛሬም ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የመግሥት ተቋማት ከወያኔ ቁጥጥር ወደ ኦህዴድ/አዴፓ ተዛውረዋል። ዛሬም በነጻ ፕረስ ሥም ጽንፍኞች (ተረኞቹ) ተደራጅተው ሀሰትና ውዥንብር ቂም በቀልና ጥላቻን በሕዝብ መሀል ይነዛሉ። ሀቀኛ ዘጋቢዎችና የሕዝብ ወገን ጋዜጠኞች ይዋከባሉ። ዛሬም ጭፍን የተረኝነት አድሎ መረኑን ለቋል።

በነጻ ገበያ ኤኮኖሚ ሥም የሀገሪቱን ዋና ዋና ብሔራዊ የልማት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ለመሸጥ አዲሱ ሹም የጌቶቹን (የዓለም የገንዝብ ድርጅት፥ የዓለም ባንክን) ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚወስደው የተሳሳተ የኤኮኖሚ ውሳኔ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አገራዊ ጥቅም አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነው። ሕዝባዊ ተቋማት በሌሉበትና በሕዝብ ተመርጦ ሕዝባዊ ቁጥጥር የሚደረግበት መንግሥት ባልተመሠረተበት ፤ አገዛዙ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጸጉሩ በጎጥ በተተበተበበትና በሙስና በተዘፈቀበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት የሆኑትን እንደ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙንኬሽንና የኢትዮጵያን ምድር ባቡር፣ … ወዘተ የመሳሰሉትን ለሽያጭ ማቅረብ አገርን ከማፍረስና በርካታ ዜጎችን ክሥራ ገበታቸው አላቆ ለሥራ አጥነት ከመዳረግ ባለፈ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሞት ለባእዳኑ ደግሞ ሠርግና ምላሽ ነው። የእነሱ/የአምባገነኖች ጥቅምና ፍላጎት ሕዝብ ከሚለው፣ ከሚፈልገው ጋር ጨርሶ አልገጥም እያለ፤ በገሀድ እየተቃረነ ሀገር እየፈረሰች ባለችበት ሁኔታ፤ ከፊት ለፊታችን የተጋረጠውን ድቅድቅ ጨለማ ብርሃን ነው በማለት የተለመደውን የአፓርታይድ የአገዛዝ ሥልጣናቸውን ለማስቀጠል ደፋ ቀና ሲሉ ይታያል። ለዚሁ አኩይ ድርጊታቸው የምዕራቡም ሆነ የአረቦች ድጋፍ አልተለያቸውም።

የዛሬዎቹ ገዥዎች (ሹሞች) የሕዝብን መፈክር ቀምተው አፍጦና አግጦ የቀጠለውን ኢዴሞክራሲያዊ አገዛዛቸውን የቃል ቅባ ቅዱስ እየቀቡ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ሥም እየማሉና እየተገዘቱ እያወናበዱ አንዳሉ ለማየት አያዳግትም። እቅጩንም ለማወቅ ሩቅ ሳንሄድ የትናንቱን የራሳችንን የአምባገነኖቹን ታሪክ በበቂ የሚያስተምረን ስለሆነ ከሚነገረውና እየተፈፀመ ካለው በስተጀርባ መጋረጃውን ገልጠን የሹሙን ተግባርና ትክክለኛ ዓላማውን፤ መመርመርና ማወቅ ይጠበቃል ብሎ ኢሕአፓ በፅኑ ያምናል። ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ . . .