በፓሪስ ከተማ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

ትላንት ህዳር 24 ቀን በፓሪስ ከተማ ያሉ ኢትዮጵያውያን በብዛት ሆነው ቤተክርስቲያኖችና ማቃጠልና ተዋህዶን ሀይማኖት ማጥቃትን በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፡፡ ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በፈረንሳይ ፓሪስ እና አካባቢዋ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጋጀ ሲሆን ተሰልፈው ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ በርካታ ፈረንሳዮች ፎቶግራፍ ከማንሳት አልፈው የሰልፉንም ምክንያት እየጠየቁ ጠቃሚ ገለጻን አዳምጠዋል፡፡ ሰልፉ ሁሉም የቤተክርስቲያኑንና የሀገሩን ጉዳትና ግፍ ለአለም የሚያሳውቅበትና ግፈኞችን የሚያወግዝበት በመሆኑ በሰልፉ የተገኙ ቀሳውስትና ምዕመናን ከሰባት ሰዓት እስከ አስራ አንድ ሰዓት ተሲዓት ይህንኑ ሲያደርጉ ታይተዋል ተደምጠዋል;፡ ሰልፈኛው ወደ ውጭ ጉዳይ በማቅናትም የሰልፉን ምክንያትና ፈረንሳይም ኢትዮጵያውያንን በመደገፍ ወንጀለኞቹን እንድታወግዝ የሚጠይቅ ደብዳቤ ሰጥተዋል፡፡ ለጀርመን ራዲዮ አማርኛ ክፍልም መግለጫ/ቃለ መጠይቅ ተሰጥቷል፡፡ ተመሳሣይ ሰልፍ ነገ ዓርብ በጀርመን በበርሊን ከተማ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምስል ከብዙ በጥቂቱ ሰልፉ የሚከተለውን ይመስል ነበር።