አሞራው በሰማይ ሲያሽ ዋለ፤ ይዤሽ ልብረር እያለ!

(በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ): በዕዳን ኃይሎች፤ አሁንም እንደ ትላንቱ፤ እንደ ሎንዶኑ 1991 ዓመተ ምህረቱ፤ የዛሬውንም ሕዝባዊ አመፅ ለማኮላሸት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ መንገንዘብ ያስፈልጋል። ወያኔን፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ ለማዳን፤ ጉጉት ይኖራቸዋል ማለት ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ዋስጥ ያላቸው ጥቅም እንዲቀጥል ስለሚፈልጉ፤ አዲስ ጥቅም አስጠባቂ ታማኞችን በማዘጋጀት ላይ እንደሆኑ ነቅቶ መጠበቅ አስፈላጊ ነው። “ወያኔ ይወገድ እንጅ፤ የፈለገው ይምጣ” የሚለው አባባል፤ “ደርግ ብቻ ይጥፋ እንጅ ማነኛው ቡድን የተሻለ ይሆናል” ተብሎ የነበረው ምኞት ምን አንዳመጣብን ሊዘነጋ አይገባውም። ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ