አረመኔያዊ ሕገ ወጥ እርምጃን በጋራ እናውግዝ

ኢሕአፓ፡  በትናንትናው እለት ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይና በሌሎች የከተማው አካባቢዎች በተቃዋሚ ድርጅቶች በተጠራው የ24 ሰአት የአደባባይ የአዳር ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት ተቃውሞቸውን ለማሰማት በተንቀሳቀሱ ዜጎች ላይ የወያኔ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ያደረሱት አፈናና አሰቃቂ ድብደባዎች ሁሉም ሰላም ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች በሙሉ በጥብቅ ሊያወግዙት የሚገባ ነው። የዚህ ዓይነት አረመኔያዊ ድርጊት ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ዜጎች ላይ ቀደም ብሎም የደረሰና ወደፊትም ሊደርስ የሚችል መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በምንም አይነት መንገድ ይህ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ…