እንጻፍ ከተባለ

ኢያሱ ዓለማየሁ፡  “የማይጽፍ ደብተራ፤ ክንፍ የሌለው አሞራ።”   ለደብተራነቱ ባልበቃም ደብተራዎችን የማወቅ ዕድል ስለነበረኝና የደብተራውን ደብተራ ጸጋዬ ገብረመድህንን ጓድ የማለቱን ዕድል አግኝቼም ስለነበር አልፎ አልፎ — ብዙውን ጊዜ “አልበዝቶም ለማለት”–ያው አጅሪዎችን የሚያንጨረጭር ጽሁፍ መጻፌ አልቀረም።  ይህም በዚያው መንፈስ ይታይልኝ።  ቁራ መቸም ባይነጣም፤ ማለትም የሚመለከታቸው መቸም የሚታረሙ ባይሆኑም ድምጽ ማሰማቱ ደግሞ ግዴታ ነው።  በተለይ ውድ ሕይወታቸውን ለሀገር በሰጡት ላይ ጸያፍ ዘለፋና ዘመቻ ሲካሂድ።   ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ