የራሱን ታሪክ የላከበረ ትውልድ፤ በራሱ ላይ ይሞት በቃ እንደፈረደ ይቆጠራል!


ከፍኖተ ዴሞክራሲ፡ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ ሬዲዮ ወቅታዊ ሐተታ፡
ከኢጣሊያ ፋሽስት ወረራ ማግስት የመጣው ትውልድ፤ አስተዳደጉ፤ በመልካም ሥነ ምግባርና አኩሪ ታሪክ ላይ በተመሠረተ ትምህርት ነበር። በዚህ ምክንያት ከአሁኑ ትውልድ የተለየ መስተጋብርና የታሪክ ግንዛቤ ነበረው። የሀገሩን ታሪክ፤ ባኅል፤ ሃይማኖት፤ የነጻነት ዋጋና ክብር፤ የዐርበኞችን መሥዋዕታዊ ትግልና ጀግንነት በሚገባ ተነግሮታል። በዚህም የተነሳ፤ የሀገር ቃል-ኪዳን አክባሪነትና የወገን ፍቅር ነበረው። ለኢትዮጵያ ሀገሩ ታላቅ ቅርስ፤ ደጀንና ተስፋ ነበር። የቀሰመውን ትምህርት እንደ መልካም አርአያ ስለሚመለከተው የሚጠበቅበትን ብሄራዊ ኃላፊነት ለመሸከም የተዘጋጀ ትውልድ እንደነበር ታሪክ ይመሰክርለታል። ያ ትውልድ፤ በራሱ ዘመን ሦስት ሥርዐት ሲፈረራርቁ ለማየት ቢችልም፤ በመሠረታዊ መልኩ ኢትጵያዊነቱን ጠብቆና አክብሮ የሚኖር ትውልድ መሆኑን በከፈለው መሥዋዕት አስመስክሯል። በመርኅ ላይ የተመሰረተ ጽናቱን ጠብቆ ቆይቷል። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …