ወያኔ አርቲፊሻል ዘረ-መልን ለገበሬዎች እንዲሰራጭ እያደረገ ነው

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ  – በኢትዮጵያ ነፃ ህክምና የሚባለው የይስሙላ መሆኑ ተጋለጠ – ወያኔ ከሱዳን ጋር የግብይት ስምምነት ማድረጉ እያነጋገረ መሆኑ ተሰማ  – ሞያሌ የታገተው ስኳር እንዲመለስ መደረጉ ታወቀ – በሐረርጌ የተከሰተው ደም መፋሰስ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴን ማሽመድመዱ ተገለጸ – ወያኔ አርቲፊሻል ዘረ-መልን ለገበሬዎች እንዲሰራጭ እያደረገ መሆኑ ይፋ ሆነ – ወያኔ፣ የበሺር ቡድንና ደቡብ አፍሪካ ከደቡብ ሱዳኑ የአማጽያን መሪ ጋር መዶለታቸው ተሰማ – ወያኔ ካለአንዳች ክስ ዘብጥያ ያወረዳቸውን ኤርትራውያን ጋዜጠኞች መልቀቁ ታወቀ – የመንገዶች መቆፋፈርና በጎርፍ መጠረግ ለትራንስፖርት ደንቃራ እየሆነ ነው ተባለ – አንድ የወያኔ ቁንጮ በገዛ ፍቃዱ ወንበሩን ለቀቀ ተባለ።

በኢትዮጵያ ነፃ ህክምና የሚባለው የይስሙላ መሆኑ ተጋለጠ

በተለያዩ ተራድኦ ድርጅቶች ማለትም በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ፣ በአውሮፓ ሕብረት፣ እና በመሳሰሉ ድርጅቶች የሆስፒታሎች ማሰፋፊያና ግንባታ ቢከናወንም ህክምና በኢትዮጵያ በእጅጉ ኋላ ቀር በመሆኑን በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች እየተተቸ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ከአጠቃላይ ሕዝብ ሰማንያ ከመቶው የህክምና ወጪውን ሸፍኖ መታከም ስለማይችል ህክምና ሳያገኝና በሽታውን ሳያውቅ በሞት የሚነጠለው ሕዝብ ቁጥር አስደንጋጭ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ የህክምና ወጪያቸውን ለመሸፈን የማይችሉ የነፃ ህክምና መፍቀዱ ቢታወቅም ይህ የህክምናውን ከሃያ እስከ ሠላሳ በመቶ ብቻ የሚሆነውን የሚሸፍን መሆኑን በሽተኞች በምሬት ሲገልጽ ይደመጣሉ፡፡ ለተለያዩ ምርመራዎችና ዋጋቸው ከሃምሳ ብር በላይ የሆኑ መድሀኒቶችን በሽተኛው እንዲገዛ ስለሚደረግ ነፃ የተባለው ለይስሙላ መሆኑን ህሙማን በምሬት ይገልጻሉ፡፡

ወያኔ ከሱዳን ጋር የግብይት ስምምነት ማድረጉ እያነጋገረ መሆኑ ተሰማ

ሁለቱ ማለትም ወያኔና የበሺር ቡድን የደረሰባቸውን የውጪ ምንዛሪ ለመወጣት በሚል ማስመሰያ አስራ ስድስት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ በሁለቱም ሀገራት ገንዘብ ግብይት ለማካሄድ መስማማታቸው ታውቋል፡፡ የሱዳኑ ፈላጭ ቆራጭ በሺር የክብር አባል በሚል ስያሜ የወያኔ-ህወሀት አባል መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት በሺር ከስልጣኑ ሲፈነገል መሸገሺያ እንዲሆነው በትግራይ የፈለገበት አካባቢ ቤተ-መንግስት መገንባት እንደሚችል ተነግሮታል ይባላል፡፡ ይህ የሱዳንና የኢትዮጵያ ገንዘቦች በሁለቱ ሀገራት ለመገበያያነት እንዲያገለግሉ መደረጉ ምስቅልቅል የኤኮኖሚ ቀውስ እንደሚያስከትልና በትሩ ይበልጥ ኢትዮጵያን እንደሚያደቅ በርካቶች ያስረዳሉ፡፡

ሞያሌ የታገተው ስኳር እንዲለስ መደረጉ ታወቀ

በኬንያ አድርጎ ዱባይ እንዲላክ የተወሰነው 44 ሺ ቶን ስኳር ሞያሌ ላይ በጠረፍ ጠባቂዎች መታገቱን ከሦስት ወራት በላይ ለበርሀ አየር ንብረት መጋለጡ የሚታወቅ ነው፡፡ ስኳሩን የጫኑት ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ ካሚዮኖች ከሦስት ወራት በላይ ሥራ መፈፍታታቸውም አነጋጋሪ ነበር ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስኳር በገጠርም በከተማም ከገበያ በመጥፋቱ ከመደበኛ ዋጋው ከእጥፍ በላይ በድብቅ እንደሚሸጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ሞያሌ የታገተው ስኳር ወደ ኋላ ተመልሶ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ መጋዘን እንዲራገፍ መመሪያ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡ ይህ በወያኔ ቁንጮዎች የተደረገ የስኳር ሌብነት በዚህ ሁኔታ መላኩ ከቆመ ስኳሩን የገዛው ዓለም አቀፍ ኩባንያ ወያኔን ፍርድ ቤት እንደሚገትረው ብዙዎች ግምታቸውን ይቸራሉ፡፡

በሐረርጌ የተከሰተው ደም መፋሰስ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴን ማሽመድመዱ ተገለጸ

ወያኔ ውስጥ ውስጡን አራግቦ በቀሰቀሰው ጦስ የንፁሀን ዜጎችን ደም ማፋሰሱና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው፣ ከቤት ንብረታቸው፣ ከወላጆቻFinote Democracy ፍካሬ ዜና መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. (08 October 2017 Weekly NEWS SUMMARY)ቸውና ከዘመድ አዝማዶቻቸው ጋር እንዲበታተኑና እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡ ይህን ወንጀል የፈጸመው አረመኔው ወያኔ ሆኖ ሳለ ደግሞ መለስ ብሎ እሱ በሕዝብ ደም የተጨማለቀ፣ ወንጀለኛ፣ ሽማግሌ አስታራቂ ሆኖ ቢውረገረግም ከሱማሌዎችም ከኦሮሞዎችም ተሰሚነትና ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውስጥ ውስጡን የበቀል ጭስ እየጤሰ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ በወያኔ ጦስ ወደ ውጪ የሚላኩ ቡና፣ ለውዝ፣ ጫት፣ ቆዳና ሌጦ፣ ሌሎችም የቅባት እህሎችና በግ፣ ፍየሎችና ግመሎች እስካሁን መስተጓጎላቸውና በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ማድረሱ ታውቋል፡፡

ወያኔ አርቲፊሻል ዘረ-መልን ለገበሬዎች እንዲሰራጭ እያደረገ መሆኑ ይፋ ሆነ

ወያኔ በበርካታ ታዳጊ ሀገራት ተቃውሞ እየገጠመው ያለውን አርቲፊሻል ዘረ-መልን ለገበሬዎች ለማሰራጨት እንደታሰበ ተሰማ፡፡ ይህ ዘረ-መል ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች እንደሚያጋልጥ በበርካታ ሳንቲስቶች በተካሄደ ጥናት የተረጋገጠ ነው ተብሏል፡፡ የዚህ የዘረ-መል ዋነኛ አምራች የሆነው ሞንሳቶ የተባለው የአሜሪካ ኩባንያ ከወያኔዎች ጋር ሲደራደር እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ምናልባትም የወያኔ ቁንጮዎችን በገንዘብ እንደደለላቸው የገመታል ይባላል፡፡ በተለይ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች የሆኑ ይህ አርቲፊሻል ዘር በቅርቡ እንዲጠቀሙ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ ከአሁን ቀደም ጥጥ ላይ በተወሰነው መሰረት ሰፋፊ የጥጥ እርሻዎች ምርቶቻቸው አርቲሻል የጥጥ ዘረ-መል በመጠቀም በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱ አልባሳት በአውሮፓ ገበያ ማጣታቸው ኩባንያዎቹ ላይ ጫና መሳደሩ የሚታወስ ነው ተብሏል፡፡

ወያኔ፣ የበሺር ቡድንና ደቡብ አፍሪካ ከደቡብ ሱዳኑ የአማጽያን መሪ ጋር መዶለታቸው ተሰማ

ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ፣ የበሺር ቡድንና ደቡብ አፍሪካ ከደቡብ ሱዳኑ ዋነኛ አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር ጋር በደቡብ አፍሪካ መዶለተቻው ታውቋል፡፡ ወያኔ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን የሳልቫ ኪርብ ቡድን ከስልጣን ለመፈንገል በርካታ ሴራዎችን ማሴሩ የሚታወቅ ሲሆን ሁሉም ከሽውበታል ተብሏል፡፡ በዚህ ደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ሴራ ላይ ተደረሰበት የተባለው ማሰሪያ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የአማጽያኑ መሪ መድርድር ስብሰባ ላይ እንዳሳተፍ ሲሆን፤ ይህ የሴራውን ሚስጢራዊነት የሚሳይ ነው ተብሏል፡፡ ወጣም ወረደ ወያኔና የሱዳኑ የበሺር ቡድን በስልጣን እስካሉ ድረስ ደቡብ ሱዳን ሰላም አይኖራትም የሚል ሀሳብ የሚሰነዝሩ በርካቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ወያኔ ካለአንዳች ክስ ዘብጥያ ያወረዳቸውን ኤርትራውያን ጋዜጠኞች መልቀቁ ታወቀ

የዛሬ አስር አመት ግድም በሶማሌና በኬንያ ድንበር አካባቢ የታገቱ ሁለት ኤርትራውያንን ወያኔ ካለምንም ክስና አንዴም የፍርድ ቤት ደጃፍን ሳያዩ አፍኖ ይህን ያህል ጊዜ አቆይቶ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በነፃ ከእስር ማሰናቱ አነጋጋሪ ነው ተብሏል፡፡ በእነዚህ ጋዜጦች ላይ በወቅቱ ወያኔ ያስተላለፈባቸው “አሸባሪዎች” የሚል ውንጀላ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በዚህ “አሸባሪ” በሚለው የወያኔ የተለመደ ውንጀላ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንኳን ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ቀርቶ ለበርካታ አመታት የታሰሩበት እንኳ አለመታወቁ አሸባሪው እራሱ ወያኔ ነው ተብሏል፡፡

መንገዶች መቆፋፈርና በጎርፍ መጠረግ ለትራንስፖርት ደንቃራ እየሆነ ነው ተባለ

ወያኔ ስለመንገድ ግንባታ ሲለፍፍ የነበረው ሁሉ ከንቱ መሆኑን መንገዶቹ በጎርፍ እየተጠረጉ መወሰዳቸው እየተናገረበት ይገኛል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በጎረፍ መቦርቦር ብቻ ሳይሆን ተጠርገው የተወሰዱ በመሆኑ በመንገዶች ዱግጓድ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከትላልቅ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ አውራ መንገዶችም ፈርስራሳቸው በመውጣቱ መንገዶቹ የጭነት መኪናዎችንና የአዎቶብሶችን ጉዞ አዳጋችና ቀርፋፋ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ በመንገዶች ገንባታና ጥገና ስም በየአመቱ በወያኔ ቁንጮዎች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚዘረፍ የአደባባይ ሚስጥር ነው ተብሏል፡፡

አንድ የወያኔ ቁንጮ በገዛ ፍቃዱ ወንበሩን ለቀቀ ተባለ

ይህ አባ ዱላ የተባለ የወያኔ ቁንጮ የወያኔ አፈ-ጉባኤነቱን መልቀቁን በደብዳቤ ማሳወቁ ታውቋል፡፡ ሰውየው በወያኔ የደም ወንጀል ከእግር ጥፍሩ እስከ እራስ ጸጉሩ የተነከረ በመሆኑ በአስራ አንደኛው ሰዐት ከወያኔ ጋር የምር ቢጣላም እንኳ ባፈሰሰው የሕዝብ ደም መጠየቁ የማይቀር ነው ተብሏል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች ይህን ጉዳይ አስመልክተው እንደሚሉት ይህ የወያኔ ፍጻሜ መጀመሪያ ሊሆን እንደሚችልና በቅርቡ የሰውየውን ፈለግ የሚከተሉ ወይም ደግሞ ወያኔ የፈጠራ ክስ መስርቶ ዘብጥያ የሚያወርዳቸው አይጠፉም የሚል ግምታቸውን ያጋራሉ፡፡ የሰውየው መልቀቅ የወያኔ የስውጥ ሥራም ይሁን ሌላ በቅርቡ የሚታወቅ ሲሆን ዋናው ጉዳይ ግን ወያኔ የነቃ ብርሌ መሆኑን የሚሳይ ነው ተብሏል፡፡

ለዝርዝር ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮን ያዳምጡ