ቀዳዳዋ ጀልባ ስትሰምጥ፤ ተሳፋሪዎቿ ይሸሿታል !

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ – የማንኛውም ሥርዓት፤ በሥልጣን የመቆየቱ ሰዓት ሲያከትም፤ አባላቱና ደጋፊዎቹ እየጣሉት sinking-TPLFበየአቅጣጫቸው ይኮበልላሉ።  ይኽ ከስተት ትላንት በደርግም ማክተሚያ ወቅት ታይቷል። የቴዎድሮስን ፈለግ እንከተላለን ሲሉ የነበሩት ሁሉ ሳይቀሩ፤ በፍርሃት ሀገሪቱን እየከዱ፤ ሕዝቡንም ለሌላ መከራ እያጋለጡ በአሳፋሪ መልክ ኮብልለዋል።  “ብልኽ አይጦች፤ መርከቧ መስጠም ስትጀምር፤ ወደ ባህሩ ይዘላሉ” እንደሚባለው፤ ዛሬም ያ ክስተት እየተደገመ በመሄድ ላይ ይገኛል።  የወያኔ ጋሻ ጃግሬዎችና የወንጀሉ ተባባሪዎች ሁሉ፤ አንድ በአንድ በየአቅጣጫቸው እየኮበለሉ ናቸው።  “ዐይተነው ጊዜ፤ ወደ አደላበት” በሚለው የጥቅመኞች / የእበላ ባዮች/ መመሪያ መሠረት፤ የነገ ሠልፋቸውን ለማሳመር ፤ ሽሽታቸውን ተያይዘውታል። “ከሞትና ከአሜሪካ ማንም አይቀርም ” በማለት በርካታዎቹ ወደ አሜሪካ በማቅናት ላይ እንዳሉ፤ የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ቆይቷል።  ሙሉውን  ሀተታ ያንብቡ