ጣኦት ጠራቢው ያሬድ ጥበቡ

ዮሴፍ ከዋሺንግተን ዲሲ – ታቦት ጠራቢው ያሬድ ጥበቡ የነበረበትን ግን ክድቶት ወደ ወያኔ ጉያ የገባው በጽናት የዘለቀውን ኢሕአፓን በመጥፎ ዓይን ቢያየው ለምን ብለን አንከራከርም። ከሕዝብ የማያቀራርበው መብቱ ነው። ኢሕአፓን ለማሳነስና እንዲያውም የለም ለማለት የፈለገው በክፋት “ጥበቡ” ነው።  “ሰራዊቱ የካቲት 23 ቀን አሲምባ ላይ የትጥቅ ትግል መጀመሩን ሲያበስር ከሁለት ቀን በኋላ ታሪካዊው የመሬት ላራሹ ታወጀ። በአዋጁ ተራማጅነትና ስርነቀል ባህሪው የተነሳ ከሳምንት በኋላ የኢህአሰ ሰራዊት ውስጥ “የመሬት አብዮት ተጠናቋል እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?’ የሚል ጥያቄ ተነስቶ ለሁለት ተከፈለ። ግማሹ አዲግራት የሚገኘው የደርግ ጦር ጋር ገብቶ እጁን ሰጠ።” በማለት ይጽፋል። ደርግ በሕዝቡና በተራማጁ ኢሕአፓ ግፊት ሳይወድ የመሬ አዋጅ አድርጓል። ችግሩ ግን አዋጁ በምንም መስፈርት ተራማጅና ስርነቀል አልነበር። አዋጁ መሬትን የመንግስት እንጅ የግለሰብ አላደረገውም። ሕዝቡ ደግሞ መሬቱ የራሱ እንዲሆን እንጅ ለመንግስት መፈንጫ እንዲሆን አልነበረም የታገለው። ለዚህም እኮ ነው ዛሬ የመሬት ጥያቄ መልስ አላገኘም የሚባለው።  ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ