ወጣቱ ትውልድና የዛሬው ግዳጁ

ዴሞክራሲያ (የኢሕአፓ ልሳን፣ ቅጽ 43፣ ቁ. 2)  – ……….. የኢትዮጵያ ሕዝብ (የትግራይ ሕዝብን ጨምሮ)፤ እሱ/ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭ የሆነባት፤ አንድነት በዕኩልነት የሰፈነባት፤ ፍትህ ብልጽግና በተግባር የሚውልባት ኢትዮጵያን ለማየት እንደናፈቀ አለ። ዛሬም የተጫነበትን የጠባብ ቡድን ኢዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከጫንቃው ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል ትግሉን እያጧጧፈ ያለው የናፈቀውን ራዕይ ዕውን ለማረግ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

ኢሕአፓም ይህን የሕዝብ ራዕይ ዕውን ለማረግ በሚደረገው ትግል እንደእስካሁኑ ከሕዝብ ጎን ቆሞ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል፤ በታኅሳስ ከዚያም በኋላ በተሰውትና ዛሬም ባደባባይ እየረገፉ ባሉ ወጣቶች፤ ባጠቃላይ ለዚያ ራዕይ በተሰው ዜጎች ስም ቃል ኪዳኑን ያድሳል።  ሙሉውን  ያንብቡ . . . . .