የህዝብን የነፃነት ጥያቄ በጠመንጃ ማፈን አይቻልም!

በዩጋንዳ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ማህበር (ኢስማዩ) . . . በመላ አለም ላይ ያሉ ለሰዎች ልጆች ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆሩና የሚሟገቱ መንግስታት፣ ሃገራትና ተቋማት እንዲሁም የዓለም መገናኛ ብዙሃን በህዝባችን ላይ የሚፈጸመው ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ከህዝባችን ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እያቀረብን በአምባገነኖች ትዕዛዝ ክቡር ህይወታቸውን ለተነጠቁ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ስንገልጽ ለዲሞክራሲና ነጻነት መረጋገጥ የህይወት ዋጋ የከፈሉ ሁሉ ጀግኖች ሰማዕታት በመሆናቸው በታሪክ መዝገብ ስራቸውና ስማቸው ህያው ሆኖ እንደሚኖር ጽኑ እምነታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።  በሰው ሃገር በስደት የምንኖር  ወገኖች የመንከራተት ዘመናችን አብቅቶ ከህዝባችን ጋር ዳግም ተገናኝተን በነጻነት፣ በፍቅርና በአንድነት እናት ኢትዮጵያን ወደነበረችበት የክብር ሥፍራ ለመመለስ እንድንችል የአምላክ ፈቃዱ እንዲሆን ከልባችን እንመኛለን። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .