“የሰከረ አሣ እንዳያመልጥህ!” የሚባልበት ወቅት ሩቅ አይደለም!

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ – ሁለት ተፃራሪ ወገኖች ዐይን ለዐይን ጠፋጥጠው ቆመዋል። በዐጥፊና ጠፊ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አንደኛው በአልሞት ባይ ተጋዳይነት በመፍጨርጨር ላይ የሚገኝ፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ከይሲ ቡድን ነው። ይኽ ቡድን፤ አዕምሮው የታወከ፤ ኅሊናው የተጨነቀ፤ የሚይዘው የሚጨብጠውን ያጣ፤ አቅመ-ደካማነቱ ከቀን ወደ ቀን እየተፋጠነ በመሄድ ላይ የሚገኝ ተቅበዝባዥ ዘረኛ ስብስብ ነው። ወትሮውንም ቢሆን እዚህ ደረጃ ሊድርስ የቻለው፤ በራሱ ኃይልና ጉልበት ሳይሆን፤ በተጻራሪ በኩል የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንዝኅላልነት፤ ካለመንጠንቀቀና ከንቀት ከመጣ የሂሳብ ጉድለት ነበር።  “የናቁት ፈረስ፤ በደንደስ” በመሆኑ፤ የተናቀው ስብስብ ይኸው ዛሬ ሕዝብና ሀገር እያጠፋ ይገኛል።  ሙሉውን  ሀተታ ያንብቡ . . .