ፍካሬ ዜና ከፍኖተ ዴሞክራሲ ሬዲዮ

ነሐሴ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. (September 04, 2016): ሕዝባዊው አመፅ እየጎለበተ ነው – ችግሮች በመባባሳቸው ምክንያት በወያኔ ላይ ያለው ምሬት እየጨመረ መጥቷል – በበአርባ ምንጭ እና በሌሎች ቦታዎች የወያኔ ጦር እየሰፈረ መሆኑ ታወቀ – በአዲስ አበባ ከተማ አፈናውና ውጥረቱ ጨምሯል – አንዳንድ መጽሐፎች እንዳይሸጡ በመከልከል ላይ ናቸው።

ዝርዝር ዜናዎች

ቅሊንቶ እስር ቤት ተነስቶ የነበረው እሳት የጠፋ ሲሆን በርካታ ሰዎች እንደሞቱና እንደቆሰሉ ተገምቷል። በወያኔ በኩል አንድ ሰው ብቻ እንደሞተና ስድስት እንደቆሰሉ ሲገለጽ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ ወገኖች ግምት ወደ 50 መድረሱ ታውቋል። በወያኔ ጥይት የተመተኑና በእሳት ተለብለው የሞቱት የሞቱት እስረኞች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ትንሽ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም ቁስለኞቹ አካባቢው ወደ ሚገኝና አንድ ሆስፒታልና እንዲሁም ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የተወሰዱ መሆናቸውና ሌሎች ጉዳት ያልደረሰባቸው እስረኞች ወደ ሌሎች እስር ቤቶች የተዛወሩ መሆናቸውን ከውስጠ አዋቂዎች ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ትችሏል። ስለእስረኞቹ ሁኔታ ለመጠቅ ወደ አካባቢው የሄዱ የእስረኞቹ ዘመዶች የታሰሩ መሆናቸውም ታውቋል።

እሁድ ነሀሴ 29 ቀን በአዲስ አበባ በሁሉም ቀበሌዎች በተጠራው የሕዝብ ስብሰባ ላይ እጅግ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው ሰው በመገኘቱ ስብሰባዎቹ ሳይካሄዱ የተበተኑ መቻላቸውን ተረድተናል፡፡ ስብሰባዎቹ ሲጠሩ የየሸማቾቹ ማህበራት ከአክሲዮን ትርፋቸው ለአባላት የሚደርሰውን ክፍያ ለመፈጸም ተብሎ የተጠራ አብዛኛው በዚህ ተታሎ በስብሰባው ያልተገኘ ከመሆኑ በቀር በጣት የሚቆጠሩ ቢገኙም በቅጥፈት በመጠራታቸው ምሬታቸውን እየገለጹ ከእየአዳራሾቹ መውጣታቸውን ተገንዝበናል፡፡

ለ2009 ዓ.ም. መቀበያ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሊካሄዱ የነበሩ የሙዚቃና የዳንኪራ ዝግጅቶች የታዳሚው ቁጥር እጅግ አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል በመገመት እየተሰረዙ በመሆናቸው ወያኔ መደናገጡ ታውቋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፉ በርካታ ድምጻውያን በአረመኔው የወያኔ ጦር የሕዝብ ደም በየቀኑ እየፈሰሰ ባለበት በዚህ ወቅት በሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ እንደማይገኙ ያስታወቁ መሆናቸውን ለዝግጅቶቹ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ለመረዳት ተችሏል፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብን ለመሸንገል ለመጪው አዲስ አመት እየተዘጋጁ ያሉትን የሙዚቃና የዳንኪራ ድግሶች ከመንግስት ካዝና እንደሚሸፈን ቃል መግባቱና እንዲሁም ዝግጅቶች መሰረዝ ሌላ ትርጉም ሊኖረው እንደሚችል በመግለጽ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ውስጥ ውስጡን እያሰራጨ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በጎንደር የወያኔ የሲቪል ባለስልጣኖች በተለያዩ ቦታዎች ባካሄዱት ሕዝባዊ ስብሰባ ከሕዝቡ በተሰጣቸው የተቃውሞ አስተያይት ተዋርደው የተመለሱ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ሳሞራ ዩኒስና ጓደኞች ወታደሮችን ሰብስቦ እርምጃ እንዲወስዱ ለሰጠው ትዕዛዝ ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰበት መሆኑ ተነግሯል። ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ከፍተኛ መኮንኖች የሆኑት ህዝባችንና ወገናችንን ገድለን ወንጀለኞች አንሆንም በማለት ትእዛዙን እንደማይቀበሉ የነገሩት መሆኑ በአካባቢው የነበሩ ወገኖች ገልጸውልናል።

ሕዝባዊ አመጹ እያመረረና እየጎለበተ መሆኑን ከየአቅታጫው ከሚደርሱን መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡ ሕዝቡ በሚስጥር እየተደራጀና እየመከረ በየጊዜው የሚወስዳቸውን ርምጃዎች በመቀያየር በተጠናከረ ሁኔታ አመጹን መቀጠሉ የኢትዮጵያ ሕዝብን አንጀት ማራሱ ሲታወቅ የዘረኛው ወያኔን ጎራ እያሸበረውና እያመሰው መሆኑ ታውቋል፡፡ የዛሬ ሳምንት እሁድ ለሁለተኛ ዙር የቀጠለው የጎንደሩ የሙት ከተማ አድማ በተሳካ ሁኔታ እንደቀጠለ ከስፍራው ከደረሰን ዜና ተረድተናል፡፡ ትግሉ አድማሱን በማስፋት በዳንግላ፣ በእንጂባራ፣ በቲሊሊ፣ በኮሶበር፣ በዱር ቤቴ፣ በመራዊና በመሸንቲ ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት ወያኔን ከማውገዙም በላይ የወያኔን ባንዲራ እያወረደ በኢትዮጵያ ሕዝባ ባንዲራ መተካቱ ታውቋል፡፡ በሁሉም ከተሞች ከፍተኛ ተኩስ እንደነበርና ከሕዝቡ የተገደሉና የቆሰሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመቱን ኗሪዎች ያስረዳሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም የሙት ከተማ አድማ በደብረታቦር እሁድ መጀመሩ ሲታወቅ በደብረ ማርቆስ በተመሳሳይ ሁኔታ ከዕሮብ እለት አንስቶ እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የተገኘው ዜና ያስረዳል፡፡ የወያኔ ነፍሰ-ገዳይ ጦር ወደ ጎንደር እንዳያልፍ ሕዝቡ ከጋይንት ደብረታቦር፣ ከደብረታቦር ወሮታ የሚወስደውን መንገድ እንደዘጋው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ማክሰኞ ወያኔ በይፋ በጎንደርና በጎጃም ሕዝብ ላይ የጦርነት አዋጁን ደልቆ ከሃያ ከባድ የወታደር መኪና በላይ ወታደሮች ጭኖ ወደ እነዚህ ስፍራዎች ማጓጓዙ ታውቋል፡፡ የጋይንት ሕዝብ የወያኔን ጨፍጫፊ ኃይል ለማሰናከል አንድ መለስተኛ ድልድይ አፍርሷል፡፡ ሕዝቡ የወያኔን የንግድ ድርጅቶች በመነጠል ጥቃቱን እየሰነዘረ መሆኑም እየታየ ነው፡፡ በአምባ ጊዮርጊስ የቱባ ወያኔዎች የግል ሀብት እንደሆነ የሚነገርለት የዳሽን ቢራን የጫነ አንድ ከባድ የጭነት መኪናን የአምባ ጊዮርጊስ ወጣቶች አስቁመው የቢራውን ጠርሙሶች አስፋልቱ ላይ ከስክሰው ዶጋ አመድ ሲያደርጉ ፕላስቲክ የቢራ ሳጥኖቹን አስፋልቱ መሀል በመከመር በእሳት አጋይተውታል፡፡

በተመሳሳይም የባህር ዳር አካባቢ ወጣቶች በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ በባእዳንና በትግራይ ተወላጆች የተያዙ ሰፋፊ የአበባ ማምረቻ የላስቲክ ድንኳን ሁዳዶችን በእሳት በማጋየት አመድ ማድረጋቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች መገለጹ ይታወቃል፡፡ ይህ ዓይነቱ እርምጃ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ብዙዎች አስተየታቸውን ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡ በመተማ ከተማ የአካባውን ወጣቶች እየጠቆሙ የሚያስገድሉና የሚሳስሩ እና የወያኔ ህወሀት አባላት ንብረት በሆኑ የንግድ ድርጅቶች ላይ ሕዝቡ ጥቃት መሰንዘሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

የመተማን ሕዝብ ለመሸንገል ሳሞራ ዩኑስና ዓባይ ፀሀይ መተማ ላይ ተገኝተው ያደረጉት ሙከራ ከንቱ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ከወያኔ አባለት ውጪ ጥሪያቸውን ተቀብሎ የተገኘ ባለመኖሩ ሁለቱ አረመኔዎች እንደ የደርጉ አረመኔ መላኩ ተፈራ ይህን ሕዝብን የመጨፍጨፍ ዘመቻን እየመሩ እንደሆነ ተረድተናል፡፡ በወንጀላቸው ላይ ወንጀል እየጨመሩ መሆኑን ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ ከአሁን ቀደም ከዚህ እንቅስቃሴ ጀርባ ሻዕቢያ እንዳለበት ሲጠቅስ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ልማትን የሚቃወሙ የቅርብና የሩቅ ጠላቶች “በጆንያ” ገንዘብ እያራገፉ ነው የሚል ክስ እየደረደረ ሲሆን ይህ ሊያሳምን የሚችለው እራሳቸው የወያኔ ቁንጮዎችን ብቻ ሊሆን እንደሚችል በርካታ ሰዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህ አባባልም በቀጥታ የሚያነጣጥረው ግብፅ ላይ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች እንደ ቋያ እሳት እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ ያለውን ትግል ለማኮላሸት ቀድሞ በ 1969 እና በ 1970 ዓ.ም. ፋሽስታዊው ደርግ በባህር ዳር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በጎንደር፣ በደብረ-ታቦር፣ በጋይንት፣ በደብረ-ማርቆስ፣ወዘተ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶችና በገንዘብ የተገዙ የየአካባቢ ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ ወጣቶችን እየጠቆሙ በማስገደል፣ በማስቀጥቀጥና በማሳሰር እኩይና አረመኔ ተግባር ላይ መሰማራታውን ተረድተናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በየጊዜው የሚገደሉ ወጣቶች ቁጥር ወደ አምስት መቶ ሊጠጋ እንደሚችል አመጹን እለት ተእለት ከሚከታተሉ ታዛቢዎች ተገንዘበናል፡፡ ወደ ጎንደርና ባህር ዳር እየዘመተ ያለው ነፍሰ-ገዳይ ጦር ከአሁን በፊት ታይቶ የማያታወቅና ፍጹም የሆነ የጭካኔ ርምጃ እንዲወስድ ጥብቅ ማስፈራሪያ የተሰጠው ለመሆኑ እያደረገ ካለው አረመኔያዊ ድርጊት መረዳት እንደሚቻል ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በተፃራሪ በርካታ የወያኔ ፖሊሶችና ወታደሮች እየተፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ ድርጊት በመሸሽ ከሕዝብ ጎን እየተሰለፉ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡ በጎንደር፣ በአምባ ጊዮርጊስ፣ በበለሳ ወዘተ. የአካባቢው ፖሊሶችና ሚሊሺያዎች ከሕዝቡ ጋር በመቆም የጠመንጃዎቻቸውን አፈሙዞች ወያኔ እያሰማራ ባለው ኃይል ላይ እያዞሩ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡ ጥቂት የማይባሉ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት የወታደሮች መክዳትና ከሕዝብ ጋር መቆም በገፍ ሊቀጥል ስለሚችል ወያኔ ቅጥር ነፍሰ-ገዳዮችን በሕዝብ ገንዝብ ተከራቶ የኢትዮጵያ ሕዝብን ለማስመታት መሞከሩ ሊጠረጠር ይገባዋል ይላሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት ሕዝባዊ አመጹ ከተጋጋለባቸው አካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የጎንደር ሕዝብ ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ለሃያ አምስት አመታት የተሸከመውን ግፍና መከራ ከጫንቃው ላይ አራግፎ ለመጣል በመሆኑ በወያኔ ፖለስ፣ በወያኔ መከላከያ፣ በወያኔ አየር ኃይልና ኮማንዶ ሠራዊት ውስጥ የሚገኙ የጋምቤላ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የሶማሌ፣ የሲዳማ፣ የኮንሶ፣ የቤንች፣ የቤንሻንጉል፣ የጉምዝ፣ የሃዲያ፣ የጎፋ፣ የቡርጂ፣ የገለብ፣ የኦሮሞ፣ የቡርጂ፣ የአገው፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ ማጂ፣ ወዘተ. ወጣቶች በወገናቸው ላይ ጥይት እንዲይተኩና የያዘዙትን አፈሙዙን የሕዝብን ገንዘብ፣ ንብረትና ደም መጠው በፈጠሙት የወያኔ ህወሀት አዛዦች ላይ መሆን ይገባዋል የሚል ምክራቸውን ማስተላለፋቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች እየፋመና እየተንበለበለ ካለው ሕዝባዊ አመጽ አስተባባሪዎቸ ከተላለፈ ማሳሰቢያ መረዳት የተቻለው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቆሙ ሀቀኛ ፀረ-ወያኔ ሕዝባዊ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ማህበሮችና ታዋቂ ግለሰቦች ለወያኔ ወታደሮች፣ ፖሊሶችና በአጠቃላይ ለወያኔ ታጣቂ ኃይሎች ሁሉ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ ተደጋጋሚ ጥሪ እንዲያደርጉ የሚል መሆኑን ነው፡፡ በተለይ ወያኔ ዘመቻ አውጆ መብታቸውን ለማስከበር በአንድነት የተነሱትን ሁሉ ያለ የሌለ የሀገር ድንበር መከላከያ ኃይልን በሕዝብ ላይ እያዘመተ እስካሁን በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎችን ደም እንዳፈሰሰና በርካቶችን ከመንገድ፣ ከመኖሪያ ቤት፣ ወዘተ. እያፈሰ ወዴት እንዳደረሳቸው ባለመታወቁ የአብዛኛው ሕዝብ ግምት እያሰቃየ በመግደል በጅምላ መቃብና በየጫካው አስከሬናቸውን የሚጥል በመሆኑ ይህንንም የፖለቲካ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለድምጽ አልባው ሕዝብ እንዲጮኹለት እያሳሰቡ መሆኑን ከተለያዩ ስፍራዎች ለፍኖተ ከተላኩ ሕዝባዊ ማሳሰቢያዎች ተገንዝበናል፡፡

በሌላ አንፃር ወያኔ ልክ ደርግ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ያደርግ እንደነበረው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስብሰባ በመጥራት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ይነዛ እንደነበረው ወያኔም በተመሳሳይ ዘመቻ እንደተወጠረ በየጊዜው መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ለትግራይ በትግራይ ሕዝብ ላይ አማራና ኦሮሞ በባእዳን ተረድተው ሊዘምቱ ነው እያሉ በመስበክ ሕዝቡ በአማራና በኦሮሞ ላይ ቂም እንዲቋጥር እያደረጉ ነው፡፡ ይህም ሞት ላይቀር መንፈራገጥ ተብሏል። ሕዝባዊ አመጹ ከተከሰተ ከአንድ ወር በላይ በማስቆጠሩ በአጠቃላይ የሀገር ኤኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሸቀጦችን በጅምላ የሚነግዱ ነጋዴዎች ገበያቸው በእጅጉ እንዳሽቆለቆለ እያስረዱ ነው፡፡ የውጪ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ የሚያስገኘው የሰሊጥ፣ የተልባ፣ የኑግ ምርት ማጓጓዝ ላይም ከፍተኛ ችግር በመፈጠሩ መስተጓጎሉ ታውቋል፡፡ ማኛውም ዓነት የትራንስፖርት መጓጓዣ ከአዲስ አበባ እስከ ደብረ-ማርቆስ ብቻ እንጅ ከዚያ እንደማያልፍ ታውቋል፡፡ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሸቀጣች በተለይ ደግሞ ናፍጣና ቤንዚን እየተስተጓጎሉ መሆናቸውንም መረዳት ችለናል፡፡ በዚህ ሳቢያም በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞችም የነዳጅ እጥረት እየተከሰተ መምጣቱ እየተስተዋለ ነው፡፡ በዚህ ሕዝባዊ አመጽ ሳቢያ የእህል፣ የጥራጥሬ እና የአትክልትና የፍራፍሬ ዋጋ በእጅጉ እየጨመረ መሆኑን ሸማቾች ያስረዳሉ፡፡ የጠፍ ዋጋ ከ2600 ብር እስከ 3200 ብር ያሻቀበ ሲሆን የሽምብራ ዋጋ 2300 ብር ደርሷል፡፡ የዋጋው መናር እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ሊቀጥል እንደሚችል ሕዝቡ ስጋቱን እየገለጸ መሆኑን ተረድተናል፡፡

ሰሞኑን በአርባ ምንጭ፣ በኮንሶ፣ በደራሼ፣ በጂንካ ሕዝቡ ወያኔ እየፈጸመ ያለውን ግፍ በመቃወም አደባባይ ይወጣል ከሚል ስጋት ወያኔ የፌደራል ፖሊስንና የመከላከያ ጦሩን በሁሉም ቦታዎች ማስፈሩ ታውቋል፡፡የተጠቀሱት ከተማዎች በአስቸኳይ ወታደራዊ አዋጅ ስር የወደቁ በሚያስመስል ሁኔታ በከተማዎቹ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የወታደራዊ ኃይል ክምችት መስፈሩ ኗሪዎችን ለጭንቀት መዳረጉን ከስፍራዎቹ የደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ በሙርሲ ቦዲ በእርሻ ልማት ስም በኦሞ ሸለቆ ዙሪያያ የሚገኙ ሰፋፊ መሬቶች ለባእዳን እና ለአገር በቀል መሬት ወራሪዎች የሙርሲ ቦዲ ገበሬዎችን በማፈናቀል የወሰዱትን መሬት ለምሳሌ የወያኔ ቀንደኛ አባል የሆነው የዶ/ር ጣዕመ ሀድጉ አምስት ሺ ሄክታር እርሻ የሚጠቀስ ሲሆን፣ እንዲመልሱ ለማድረግ የአካባቢው ሕዝብ በጊንዲላና በድንጋይ መንገድ በመዝጋት ወያኔ ተጨማሪ ነፍሰ ገዳይ ኃይል ወደ አካባቢው እንዳያስገባ እየተከላከሉ መሆናቸው በስፋት ይነገራል፡፡ የኮንሶ ሕዝብ እያቀረበ ያለው የአስተዳደር መዋቅሩ ከጉማይዴ ጋር መሆኑ ከስነምራዊ አቀማመጥና የኮንሶ ሕዝብን ባህልና ቋንቋ ለማሳደግ እንቅፋት መሆኑን በመጥቀስ እያደረገ ያለው ጥያቄ በተደጋጋሚ በወያኔ ሹሞች ውድቅ በመደረጉ ሕዝቡ እያቀረበ ላለው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እስካላገኘ ድረስ በኮንሶ መሥሪያ ቤቶች ሁሉ ዝግ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከስፍራው ከደረሰኝ መረጃ መረዳት የተቻለው በርካታ የኮንሶ ወጣቶችና ጎልማሶች በየጊዜው እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ መሆኑን ነው፡፡ አሁን በኮንሶ እየደረሰ ያለው ውሎ አድሮ በሌሎችም እንደሚደርስ ምንም ጥርጥር እንደሌለው ወቅታዊውን ሁኔታ በአንክሮ የሚከታተሉ ወገኖች እገለጹ ነው፡፡

በየምሽቱ በአዲስ አበባ ድንገተኛ ፍተሻ እየካሄ ነው፡፡ መንገድ ተዘግቶ ተሸከርካሪዎችንና እግረኞችን አንድ በአንድ አሰልፈው እየፈተሹ ነው፡፡ ፍተሻዎቹ እየተካሄዱ ያሉት ማታ የአዲስ አበባ ኗሪዎች ከሥራ ወደ መኖሪያ ቤቶቻቸው በሚመለሱበት ወቅት ሲሆን የተፈተሹ ሰዎች ሲያስረዱ በትከሻ የሚነገት ቦርሳንና ሰውነትን አበጥረው ለመፈተሽ በሚያደርጉት ጥረት የተሸከርካሪና የእግረኛ ሰልፍ መንገዶች መዝጋት ደረጃ ላይ መድረሱን ያስረዳሉ፡፡ እስካሁን ከአዲስ አበባ በርካታ ወጣቶች እየታፈኑ እየታሰሩ እንደሆነ ተረድተናል፡፡ የታሰሩባችድው ቦታዎች የማይታወቁ ሲሆን በይስሙላው የወያኔ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከሃያ ቀናት በላይ ያስቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ከሺ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ ፍተሻዎቹ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ከፈታሽ ፖሊሶቹ ጋር አብረው በመሆን የሚፈተሹ ሰዎችን በዓይነ ቁራኛ የሚታተሉ የወያኔ ደህንነቶች እንዳሉም ተገንዝበናል፡፡ አንዳንዴ የሚጠረጠሩ ሰዎችን መታወቂያ በመጠየቅ መታወቂያቸው ላይ የብሔረሰብን ማንነት በማየት ከተፈታሶች ዞር እደረጉ በተለይ አማራ ወይም ኦሮሞ የሚል ከሆነ በደህንነቱ ሠራተኛ ውሳኔ ታፍነው የመወሰድ አደጋ ያጋጠማቸው እንዳሉም ከዓይን እማኞች መገንዘብ ተችሏል፡፡

ወያኔ መፀሐፍ አዟሪዎችን እያሰረና አንባቢ እጅ እንዳይገቡ የሚፈልጋቸውን መፀሐፍትን እየነጠቀ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በየመንገዱ መፀሐፍ እያዞሩ የሚሸጡና እግረኛ መንገድ ላይ መፀሐፍት ዘርግተው የሚሸጡ ወጣቶችን የወያኔ ፖሊሶችና ደህንነቶች እያሳደዱ በማሰር ላይ መሆናቸውን ተረድተናል፡፡ በመፀሐፍ ማዞር የእለት ጉርሳቸውን የሚያገኙ ወጣቶችን የወያኔ ፖሊሶች ከማሰራቸውም በተጨማሪ በሰደፍና በእርግጫ ቁም ስቅላቸውን እንዳሳይዋቸው ግፍ የተፈጸማባቸው መፃሕፍት ሻጮች በምሬት ያስረዳሉ፡፡ በይፋ አንባቢ እጅ እንዳይገቡ በወያኔ እየታፈኑ ካሉት መፀሐፍት መሀል በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የተደረሰው “የኦሮሞና የአማራ የዘር ግንድ” ፣ በቂሊንጦ ታስሮ የሚገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መፀሐፍ “የፈራ ይመለስ” እና የጋዜጠኛ ሙሉ ቀን ተስፋው “የዘመኑ ጥፋት” የሚሉት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ መሆናቸውን ተረድተናል፡፡ እየተወረሱ ያሉት መጻህፍትም በእሳት እንደሚቃጠሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ከሦስቱ አንዱ መፀሐፍ የተገኘበት መፀሐፍ አዟሪ በጹኑ እንደሚደበደብና እንደሚገላታ ተረድተናል፡፡ የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ መፀሐፍ የሁለቱ የአማራና የኦሮሞ ብሔረሰብ ከአንድ የዘር ግንድ የመነጩ መሆናቸውን ስለሚያትት በዚህ የተነሳ በቅርቡ በጎንደር በተደረገው ሰልፍ ላይ በተንጸባረቀው የአንድነትና የብሐራዊ መንፈስ የተደናጠው ወያኔ ይህ መፀሐፍ በስፋት ከተሰራጨ ይህን የአንድነት መንፈስ የማጠናከር አንዳች ኃይል ይኖረዋል የሚል ስጋት እንዳደረበት መፀሐፉን ያነበቡ አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ፡፡ ወያኔ ለይስሙላ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን መቀበሉን ቢያትትም ማሰብ፣ መናገር፣ መፃፍ፣ መወያየት፣ መሰብሰብ፣ መሰለፍ፣ በማህበር መደራጀት፣ ወዘተ. ወንጀል እንደሆኑ በተግባር እያሳየ ለመሆኑ ይህ ዓይነተኛ ምሳሌ መሆኑን የፖለቲካ ተቺዎች የወያኔን ፀረዴሞክራሲነት እየኮነኑ ያስረዳሉ፡፡

ዝርዝር ዜና ያዳምጡ