አሳዛኝ የክህደት ተግባር

ከስዊድን የተላከ ሌላ ደብዳቤ: … ገሞራውን ይበልጥ ሲያሳዝነው የኖረው ግን የባዕዳኑ በደል አልነበረም። ዋነኛው ህመሙ ከሃዲና ከርሳም የኛው አገር ሰዎች ሲፈጽሙበት የኖረው በደል ነው። ገሞራው የሚያምነውን በግልጥ ነግሮ የሚሄድ እንጂ ቂመኛና ተበቃይ አልነበረምና ሊጐዱት፣ ሊያጠቁት ስለተነሱ ሰዎች እንኳን መጥፎ ሲነገር መስማት የሚከብደውና ተዉ ብሎ የሚመክር ታላቅ ሰው ነው። ሲበዛበት ግን ተዉ እንጂ ማለቱ አልቀረም። ከአስር ዓመታት በፊት እየጉነታተሉ ያስቸግሩትን ክፉ ’ሰዎችን’ በአንድ በወቅቱ በአገር-ቤት ውስጥ ይታተም በነበረ መጽሄት ባወጣው ጽሁፍ የድርጐ ጥገቶችና የመኢሶን አባ ሽሜ ጉጉዎች እረፉ’ንጂ በማለት መቆንጠጡ አንድ አብነት ነው። አሁን ክቡር ሥሙንና ዓላማውን ያረከሱ መስሏቸው አስከሬኑን ለወያኔ አገዛዝ እጅ መንሻ አድርገው ካቀረቡት ከንቱዎች ገሚሱ ያኔ በቁጣው ቆንጥጦ ካንጫጫቸው ሰዎች መካከል ናቸው። የዚህ የአሁኑ የአስከሬን ደላላዎች ስብስብ የተለየ የሚያደርገው ስብጥሩ ነው።  ሙሉውን ያንብቡ …