ታኅሣሥና ሰማዕታቱ ሲዘከሩ!

ዴሞክራሲያ (የኢሕአፓ ልሳን) ቅጽ 40፣ ቁ. 3 (ታኅሣሥ 2007 ዓ. ም.)፡ በየዓመቱ የሚመጣው ወረሀ-ታኅሣሥ፤ ለኢትዮcandleጵያ ሰማዕታት መዘከሪያና ታሪካቸውንም ማክበሪያ በመሆን በመላው ታጋይ ዘንድ በአክብሮት ተዘክሮ የሚውል ወር ነው። የሰማዕታቱ የጀግንነትና የቆራጥነት ታሪክ ይታወሳል። ይወደሳል። ይቀደሳል። ትግሉንም የቀጠለው ኃይል ፤ የትግሉን ቃል-ኪዳን የሚያድስበት ወር ነው። ለአዲሱና ለተተኪው ትውልድም ትምህርት ማስተላለፊያ መድረክ ነው። ተተኪ የሌላት ሀገር በመሆኗ፣ በዘለዓላማዊነቷ ፀንታ የምትኖር ኢትዮጵያ መሆኗ ባይካድም፤ ትውልዱ ግን እየተተካ መሄዱ፤ የታሪክ ሐቅና የተፈጥሮ ሕግ መሆኑ አያከረክርም። ለቋሚቷ ሀገር፣ ቋሚ የሆነ አኩሪ ታሪክ አስመዝግቦ ማለፍ፤ የቱን ያህል አኩሪ መሆኑን የታኅሣሥ ሰማዕታት በደማቸው ጽፈው አልፈዋል። በህልፈታቸውም ህያው መሆናቸውን አስመስክረዋል። በመስዋዕትነት ማለፍ ህያውነት እንጅ ኅልፈት እንዳልሆነም አስተምረው ነው ያለፉት። መሥዋዕታዊ ኅልፈት፤ መሞት ሳይሆን ህይወት ስለሆነ፣ ለታህሣሥ ጀግና ትውልድ አፅም፤ ዘለዓለማዊ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን። ሙሉውን ያንብቡ …