ዝምታ ለበግም አልበጃት!

ዴሞክራሲያ (ቅፅ 41 ቁ. 4):  አምባገነኖች ሥልጣንን ለመቆናጠጥ የሕዝብን ፈቃድ ወይም ድጋፍ ፈልገውና ጠይቀው አያውቁም።  የሚፈልጉት የሕዝብን ታዛዥነትና ጸጥ -ለጥ ብሎ መገዛትን ነው።  የሕዝብን ፍላጎት ሰምተው፤ የልቡን ትርታ አዳምጠው፤ ፍላጎቱን ተከትለው፤ አግባብተውና በጋራ አቅጣጫ ላይ ተመሥርተው ማስተዳደርን አያውቁበትም።  የበታችና የበላይ ሰልፍን የሚያረጋግጡት በኃይል ወይም በጠብ-መንጃ ብቻ ነው። በኃይል በመቀጥቀጥ ካልገበርክ፤ ተቃውሞህን ካላቆምክ፤ የባሰ ይመጣብሃል በማለት “ማሸማቀቅ” ሰብዓዊ ክብርን መግፈፍና ማዋረድ የአምባገነኖች ተፈጥሯዊ መለያችውና ባህሪያቸው ነው።    ሙሉውን ያንብቡ