የትግል አቅጣጫ ጉዳይ በአግባብ አልተያዘም

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (ሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ):   የኢትዮጵያን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት አምስት እርምጃ ወደ ኋላ በሚል መርህ ሊመሩት የሚፈልጉ ክፍሎች እንዳሉ የምናውቀው ዛሬ አይደለም።  በተከታታይ ዋና ጉዳዮች ሆነው፤ዋና የትግሉ ጥያቄዎች እየሆኑ አለአግባብ የተያዙትን (የድርጅት ጥያቄ፤ የህብረት ጥያቄ ወዘተ.. ) በሚመለከት አስፈላጊውን እርማት ለማድረግና ትግላችን አቅጣጫውን እንዳይስት ለመከላካል ጥረናል።  በዚሁ በመቀጠል የስደት መንግስት ወይም የሽግግር መንግስት ዛሬ እናቋቁም ከሚለው የተሳሳተና ከንቱ አቅዋም ጋር ልዩነታችንን እንገልጻለን።  የዚህ ሀሳብ አቀንቃኞች ከታሪክም ሆነ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ምንም ትምህርት ያልቀሰሙ መሆናቸውን መረዳትም ከባድ እይደለም።  ሙሉውን ያንብቡ