የኢሕአፓ አባላት እና ደጋፊዎች በስቶክሆልም ከተማ የወያኔ ኤምባሲን ለተወሰነ ጊዜ ይዘው ቆዩ

ሰበር ዜና፡  በዛሬው ዕለት (ሴፕቴምበር 30 ቀን 2014) ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በስቶክሆልም ከተማ የወያኔ ኤምባሲን ለተወሰነ ጊዜ ይዘው ቆዩ።  ተቃውሞውን ያዘጋጁት በኖርዌይ የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ፣ የሴቶች ክንፍ እና ደጋፊ ኮሚቴ ኣባላት መሆናቸውም ታውቋል።  ወያኔ የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች አባላትን በሰበብ አስባቡ እየከሰሰም ቢሆን አስሮ እንደያዛቸው ሲያሳውቅ፣ ገና ከጠዋቱ የሚያራምደውን ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ሕዝብ አቋም በመቃወም የታገሉትን ፋና ወጊ የኢሕአፓ አመራሮችና አባላትን አፍኖ፣ አሁንም እያፈነ ዬት እንዳደረሳቸው አለመታወቁን በመቃወም ነበር ዝግጀቱ የተቀናበረው።  ተቃዋሚዎቹ ኤምባሲው ውስጥ በመግባት የጓዶቻቸውን ደብዛ መጥፋት እና ሌሎችንም መሪ መፈክሮች ሲያስተጋቡ የወያኔው ኤምባሲ ሠራተኞች በድንጋጤና ፍርሃት ርደው ነበር።  በሎሌነታቸው ሊያሳዩት የፈለጉት መኮፈስ ጥሏቸው ሄዶ መግቢያ ነው ያጡት።  ተቃዋሚዎቹም አምባሳደር ተብዬዋ መጥታ ካላነጋገረችን እና ጌቶቿ ገዢዎች ”ጓዶቻችንን ዬት እንዳደረሱዋቸው ለጥያቄያችን መልስ ካልሰጠችን አንወጣም!” ብለው ኤምባሲውን ለአንድ ሰዓት ይዘው ቆይተዋል።  ሰሞኑን ወያኔ በዓባይ ግድብ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ ባዘጋጀውና አድር ባዩ ንዋይ ደበበ ባቀንቃኝነት በተገኘበት ጭፈራ ላይ የክብር ታዳሚ ለመሆን ስትመጣ፣ በኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በተወረወሩ ዕንቁላሎች ቀልቧ የተገፈፈው አምባሳደር ተብዬዋም  የኢሕአፓ አባላት እና ደጋፊዎች ጥያቄን በተመለከተ ፊት ለፊት ለማነጋገር ድፍረቱን አላገኝችም።  በፖሊሶቹም በኩል የኢትዮጵያዊያኑ ጥያቄ ቀርቦላት ”አሁን መልስ ልሰጥ አልችልም በቀጠሮ ካልሆነ” ስላለች፣ ፖሊሶቹ ጉዳዩን ተከታትለው ለእናት ድርጅታቸው ለኢሕአፓ  የክትትላቸውን ወጤት እንደሚያሳውቁ ቃል ገብተውላቸዋል። የተፈቀደው የተቃውሞ ሰዓት ሲያልቅም ኢትዮጵያውያኑ ወደሚኖሩበት ሀገር በሰላም ተመልሰዋል።  ቪዲዮ ይመልከቱ…