“የኢትዮጵያ ጠላት ማነው ነው?” ተብሎ በተደረሰው መጽሐፍ ላይ አስተያየት

ከእውነቱ ፈረደ (ደቡብ አፍሪካ)፡  ኢትዮጵያ ውስጥ በሥልጣን ላይ የነበሩት መንግሥታትና አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኘው ዘረኛ የወያኔ መንግሥት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመጨቆን መሳሪያ አድርገው የተጠቀሙት ከሕዝብና ከአገር ጥቅም ራሳቸውን የሚያስቀድሙ ግለሰቦችን በመጠቀም የውሸት መረጃዎችን ለሕዝብ በማስተላለፍ ነበር/ነውም።  ወያኔ በሥልጣን መንበር ተቀምጦ ሕዝብን መጨቆን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚከፋፍሉ፣ ሕዝቡ ለመብቱና አገሪቱን ከጠላት ለመከለከል ያደረጋቸውን ትግልና መስዋዕት ከንቱ የሚያደርጉ ብዙ መጸሕፍት ተጽፈዋል።  ጥቂት ደግሞ በእውነት ላይ ቆመው ለአገር፣ ለሕዝብ የሚጠቅሙ መጻሕፍት በሀቀኛ ጸሓፊዎች ለሕዝብ ቀርበዋል። እነዚህ ሊመሰገኑ ይገባል።  ከእውነት ርቀው ለህዝብና ለወጣቱ ትውልድ ትክክለኛ ያልሆነ ታሪክ ለማስተላለፍ ለሚጥሩት ግን ተው ማለት ያስፈልጋል።  በዚህ መንፈስ ነው “የኢትዮጵያ ጠላት ማነው?”  በሚል ርዕስ በጄኔራል በኃይሉ ክንዴ በተጸፈው መፅሀፍ ላይ አስተያየቴን ለመሰንዘር የተገደድኩት። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …