(ከአባይ መንግስቱ፣ ቻላቸው ዓባይ፤ ጐሹ ገብሩና፣ አብዩ በለው) – ”ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” የሚለው “ሊበሏት ያሰቧትን…” አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው ከማን በኩል እንደሆነ ማወቅ “ሊበላን” ያሰፈሰፈውን አስቀድሞ ለማወቅ ይረዳል የሚል እምነት አለን። ከዚህም በመነሳት ባደረግነው ጥናትና ክትትል ጥያቄው ተደጋግሞ የሚነሳው በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ሲሆን ይህ ወራሪና ተስፋፊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የወልቃይትን መሬት በረገጠ ወቅት በአቶ ስብሃት ነጋ አዛዥነት ና በአቶ መኮንን ዘለለው አጥኝነት ጥያቄው ለወገናችን ቀርቦ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለዚህ እኩይ ቡድን በተንበረከኩና ባደሩ፤ ይልቁንም የዚህን ወንጀለኛ ቡድን በህዝባችን ላይ የፈጸመውን የዘር የማጽዳት ወንጀልና በሃይል ወደ ትግራይ የከለላቸውን የጎንደር ታሪካዊ ለም መሬቶች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት በሚዋትቱ ጥቂት ተንበርካኪዎች በኩል ጥያቄው ዳግም ሲነሳ እየሰማን ነው:: ሙሉውን ያንብቡ …