“ከዛ ትውልድ ለዚህ” – አዲስ የትግል ገድል ታሪክ መጽሀፍ በገበያ ላይ

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  የ ያ ትውልድ መፅሃፍ በገበያ ላይ ውሏል!! ለህዝቦች እኩልነት፣ መብትና ዲሞክራሲ በፅናት ሲታገሉ  የተሰዉት፣ ደብዛቸው የጠፋትን፣ አሁንም በትግል ላይ ያሉትን የኢሕአፓ አባላት  አጫጭር እውነተኛ ታሪክ ትምህርታዊ በሆነ መንገድ ይዞ ቀርቧል። bookተመዝግቦ የተቀመጠ እውነተኛ ታሪክ በራዦችን ለመዋጋት ፍቱን መሳርያ ነው። አዘጋጁ መኮንን ተስፋዬ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ላይ አሜሪካና  ካናዳ ውስጥ  በተለያዩ  የኢትዮጵያዊያን ንግድ ቤቶች ውስጥ መጽሀፉ በሽያጭ ላይ መሆኑን አሳውቋል።  የደብተራው ድረ-ገጽ አዘጋጆች፣ ለመኮንን ድንቅ ስራ ነው፣ እንኳን ደስ ያለህ እንላለን።