ወያኔን፣ መንግሥት ነው ማለት ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው!

ዴሞክራሲያ ቅፅ 40 ቁ. 9 (ሰኔ 2007 ዓ.ም):  ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደማንኛውም ሀገር ብዙ ነገሮች ወደፊት እየገሰገሱ ባሉበት የ21ኛው ክ/ዘመን ውስጥ ትገኛለች።  አዎ ከምንቆጥርበት የጊዜ ስሌትና የለውጡና የእድገቱ ተጠቃሚ ከሆኑ የሌሎች አገር ዜጎች ከሚያስቡት ውጭ ማሰብ ስለማንችል ለኛም ዘመኑ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው።  ውስጡ ያረጀ ቤት ነገ እንደሚፈርስ እየታወቀ ላዩን በቀለም እንደሚያሳምሩት ሁሉ በሕዝባችን ላይ በገዥነት የተሰየሙባት፤ ለዓይን የሚስብ የሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ቀለም የተቀቡ “መንግሥት” ተብየዎች አስተሳሰብና ተግባር ግን ቀደም ብለው ከነበሩት መሳፍንትና ኋላ ቀር አምባገነኖች ጋር የሚመሳሰል ነው።  አምባገነናዊ መሳፍንቶች ናቸው እንበል? ይህንን ደግሞ እንዲሁ ለማለት ብቻ የሚቀርብ ሳይሆን ቀደም ባሉት አገዛዝም ሆነ በተለይም ባለፉት 24 ዓመታት በግልጽ ወገናችን በዐይኑ በብረቱ ያየው፣ በደም ባጥንቱ የኖረው ጉዳይ ነው። ሙሉውን ያንብቡ